#Ethiopia #EthioMuslims #DY #JumaDemonstration የጁምዓ - TopicsExpress



          

#Ethiopia #EthioMuslims #DY #JumaDemonstration የጁምዓ ተቃውሞ መርሐግብር! ሐሙስ ሐምሌ 25/2005 ቅድመ ዝግጅት 1. ‹‹ዛሬም የሚሊዮኖች ድምጽ ታፍኗል›› የሚል ወረቀት ሁሉም በነፍስ ወከፍ አትመን ይዘን እንመጣለን፡፡ 2. የትራንስፖርት እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል በጊዜ ጉዞ መጀመርና ትራንስፖርት ካልተገኝ በእግራችን ተጉዘን ቀድመን ፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ መገኘት ይኖርብናል፡፡ መርሐግብር * ሶላት እንደተጠናቀቀ ባለንበት ቦታ በመንበርከክ መሪዎቻችንን ማሰር የወከላቸውን ህዝብ ማሰር መሆኑን ለማሳየት እጃችንን ወደ ላይ ከፍ በማድረግና እርስ በእርስ በማቆላለፍ ለ 5 ደቂቃ፡፡ * በመቀጠል እንቆምና አንድነታችንን ለማሳየት ትከሻ ለትከሻ ተገጣጥመን መንግስት የህዝብን ድምጽና ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በሃይማኖታችን ጣልቃገብነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ለማውገዝ አፋችን ላይ ፕላስተር በማድረግ ይዘነው የመጣነውን ‹‹ዛሬም የሚሊዮኖች ድምጽ ታፍኗል›› የሚለውን ወረቀት ለ 5 ደቂቃ ከፍ አድርገን እናሳያለን፡፡ * በክልሎች በተለመዱት የተቃውሞ ቦታዎች የምናደርጋቸው ተቃውሞዎች እዚሁ ላይ ከተጠቀሰው ጋር ተመሳሳይ ሆነው እንደየአካባቢው ሁኔታና ባህሪ የአተገባበር ለውጥ እና ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ * በመጨረሻም የፆመኛ ዱዓ አላህ ዘንድ ተሰሚነት ያለው በመሆኑ ሁላችንም ከልባችን አላህ የመጣብንን መከራ እንዲያነሳልን፣ አገራችን ሰላም እንድትሆንነና የታሰሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያደርግልን ዱዓ በማድረግ፤ እንዲሁም ለምስኪኖች የምንችለውን ያህል መጽውተን በሰላም ወደየአካባቢያችን እንመለሳለን፡፡ * ማስታወሻ - በተቃውሞአችን እለት በመስጂድ ውስጥ ያለንም ሆነ ከመስጂዱ ውጪ የምንገኝ ባለንበት ቦታ ረግተን በመቆም የምልክት እና የዝምታ ተቃውሞአችንን ማከናወን ይኖርብናል፡፡ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስን በማስቀረት ባለንበት ቦታ መርገት ይኖርብናል፡፡ ይህም በመሀላችን ሰርገው በመግባት ሁከትን ለሚሹ የትንኮሳ ክፍተቶችን ለመዝጋትና ወጥነት ያለው አብይ ተቃውሞ ለማድረግ ይረዳናል፡፡ የተለመደው ሰላማዊነታችንና ጥንቃቄያችን አይለየን፡፡ የተቃውሞ መርሐግብሩን እንዳጠናቀቅንም ተነጥለን ከመመለስ በጋራ ሰብሰብ ብለን ወደመጣንበት መመለስ እንዳለብንም ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ አላሁ አክበር! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና አዲሱ ገጻችንን ላይክ ያድረጉ! https://facebook/DimtsachinYisema2
Posted on: Thu, 01 Aug 2013 07:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015