#Ethiopia #ProtectYourself መንግስት እንዳሻው - TopicsExpress



          

#Ethiopia #ProtectYourself መንግስት እንዳሻው የሚያዘውን ኢትዮ ቴሌኮንምን ተጠቅሞ ስልክህን እንዳሻው ይጠልፋል፣ በኢንሳን እስራኤሎችን ቻይናዎችንና እነ ፊሽ ፊሸርን የመሳሰሉ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር የወጣባቸውን ሶፍትዌሮች ተጠቅሞ ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ አራማጆችን፣ የሰብዓዊ መብት ታጋዮችን፣ የእምነት መሪዎችን እና ይቃወሙኛል ያላቸውን ሁሉ ይሰልላል ብዙዎች እዚህ ግባ በማይባሉ ነገሮች ተከሰው እናያለን የመንግስትን ሃጢአት መናገር ወንጀል የሆነበት አገር አድርጓታል ኢሕአዴግ፤ ለማንኛውም መንግስት ከአፋችን ነጥቆ እኛኑ ለማፈኛ ሚሊዮን ዶላሮችን ሲያወጣ እኛ ምንም የለንም ብለን በኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶቻችን እንደፈቀዳቸው እንዲሆኑ መፍቀድ የለብንም፡፡ እናም እንደ Detekt ያሉ ሶፍትዌሮችንና ሌሎችን ስናገኝ ራሳችንን ለመጠበቂያነት እንጠቀምባቸው፡፡ ይሄንንም ለመጠቀም እባካችሁ አትስነፉ፤ ተቃዋሚዎችንና አክቲቪስቶችን መርዳት የምትፈልጉ ልታደርጓቸው ከምትችሏቸው ነገሮች አንዱ የአንቲ-ቫይረሶችን ላይሰንስ ገዝቶ በመላክ የበኩላችሁን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ሌላው መብታችሁ ቢሆንም አምባገነኑ መንግስት ያለእፍረት እንደማስረጃ ሊጠቀምበት ይችላል የምትሏቸውን ቻቶችና መረጃዎች ከኮምፒተራችሁ አጥፉ፡፡ Detektን መጠቀም የፈለጋችሁ በሊንኩ ታገኙታላችሁ፡፡ https://resistsurveillance.org/#
Posted on: Thu, 20 Nov 2014 14:55:18 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015