A Draft Law that Appoints a Representative for the Patriarch is - TopicsExpress



          

A Draft Law that Appoints a Representative for the Patriarch is Being Discussed - ለፓትሪያርኩ እንደራሴ እንደሚመደብ የሚገልጽ የህግ ረቂቅ ለውይይት መቅረቡ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ፓትሪያርኩን የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽ እና የፓትሪያርኩን ሓላፊነትና ተጠያቂነት በጉልህ የሚሳዩ አንቀጾችን ባካተተ የህግ ረቂቅ ላይ እየተወያየ እንደሆነ አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ይህ የተገለጸው ከባለፈው ረቡዕ ጀም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ በ1991 ዓ.ም ህገ ደንብ ማውጣቷን ያስታወሰው ዘገባው አዲሱ የሕግ ረቂቅ ከሌሎች ህጎች እና ከቤተክርስቲኒቱ እድገት እና ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ መዘጋጀቱን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ዘገባው እንዳመለከተው በአዲሱ የሕግ ረቂቅ አንቀጽ 24 ላይ የተመለከተው ሃሳብ ፓትሪያርኩ የተጣለባቸውን ሓላፊነት እና መንፈሳዊ አመራር በሚጠይቀው ብቃት እና ደረጃ ለማከናወን እንዲችል የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ ሲሆን የእንደራሴው ምርጫም በፓትሪያርኩ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በሚጠቆሙ ሶስት ዕጩዎች የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ብቻ በሚሳተፉበት ምርጫ እንደሚከናወን ይገልጻል፡፡ የሚመረጠው እንደራሴም እሜው ከ50 እስከ 60 የሆነ እና የአስተዳደር ችሎታ እና መንፈሳዊ አመራር ልምድን፣ መንፈሳዊ እና ዘመናዊ እውቀትን አጣምሮ የያዘ ሊሆን እንደሚገባውም በረቂቅ ህጉ ተመልክቷል፡፡ ዘገባው በጉባኤው የእንደራሴውን አስፈላጊነት የሚቃወሙ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ‹‹ ግለሰባዊ ስልጣን ፈላጊነት ስሜት የሚገንበት ፣ የፓትሪያርኩን ስልጣን የሚጋፋ እና መካሰስን የሚያበረታታ ነው›› በሚል ሃሳባቸውን ማቅረባቸው የገለጸ ሲሆን የእንደራሴው አስፈላጊነት ግድ ከሆነም እንደራሴው በፓትሪያርኩ ጥቆማ ብቻ መመረጥ እንዳለበት የቃሉ ትርጉም እንደሚያስገድድ በመግለጽ ተከራክረዋል ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ፓትሪያርኩ በቤተክርስቲያኒቱ ታላላቅ በአላት ላይ እንደ አሰስፈላጊነቱ እየተገኙ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ የሚሠጡት እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን መንፈሳዊ መልእክት የሚያስተላልፉት በሃገሪቱ የስራ ቋንቋ ብቻ እንደሚሆን በህግ ማሻሻያ ረቂቁ ላይ መስፈሩም ተጠቅሷል፡፡ More Here...diretu.be/547782
Posted on: Mon, 19 May 2014 08:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015