Chinese Premier Li Keqiang to Visit Ethiopia ... See at ... - TopicsExpress



          

Chinese Premier Li Keqiang to Visit Ethiopia ... See at ... diretu.be/874332 | የቻይና ጠ/ ሚ ሊ ኬኪያንግ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ከመጪው ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው። ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ውስጥ በቻይና መንግሥት እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀክቶች መጎብኘትን ያጠቃልላልም ነው የተባለው፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት ፥ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያና ቻይና ሁለገብ የሆነ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ማዕከል ያደረገ ግንኙነት ኤአ ከ1970 ጀምሮ መመስረታቸውንም ነው አምባሳደሩ ያወሱት። ቻይና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በግንባታው ዘርፍ የኢትዮጵያ ዋንኛ አጋረ መሆኗንና በአገሪቱ ኢንቨስት በማድረግም ህንድንና ቱርክን በማስከተል ቁጥር አንድ ቦታን ይዛ እንደምትገኝ ይታወቃል። ባለፈው ህዳር ወር በቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር የተመራ ልዩ ልዑክ በኢትዮጵያ ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው።(ኤፍ.ቢ.ሲ)
Posted on: Tue, 29 Apr 2014 12:30:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015