EthioTelecom to Implement Network Assessing Robots ...See at ... - TopicsExpress



          

EthioTelecom to Implement Network Assessing Robots ...See at ... diretu.be/563233 | የኔትወርክ ጥራት ደረጃን የሚለኩ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶች ሥራ ላይ ሊውሉ ነው ተባለ ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ስልክ አገልግሎት ጥራትን በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ የሚፈትሹ በተሽከርካሪ ላይ የሚገጠሙ ተንቀሳቃሽ ሮቦቶችን ሥራ ላይ ሊያውል እንደሆነ ያስነበበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ የሚገኘው የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ሥራ ላይ የሚውሉት የኔትወርክ ጥራት መፈተሻ ሮቦቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የሚያጋጥሟቸውን የኔትወርክ ጥራት ጉድለቶች በትክክል መገንዘብ የሚችሉ መሆናቸውን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዱዓለም አድማሱ ተቅሶ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የሚያጋጥማቸውን የጥራት መጓደል፣ መቆራረጥ፣ የራስን ድምፅ መልሶ መስማትና የመሳሰሉትን አሁን በሥራ ላይ ያለው ሲስተም አይገነዘብም የተባለ ሲሆን በአዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እነዚህን ሮቦቶች በማንቀሳቀስ እርስ በርስ ጥሪ እንዲለዋወጡ በማድረግ የሚያጋጥማቸውን የኔትወርክ ጥራት ጉድለት መለየትና በፍጥነት ችግሩን የመቅረፍ ሥራ ለማከናወን ያስችላሉ እንደሚስችሉ ተገልጿል፡፡ ‹‹ሮቦቶቹ የት ቦታ የድምፅ ማስተጋባት እንደገጠማቸው የት ቦታ ድምፃቸውን መልሰው እንዳዳመጡ፣ የት ቦታ ያደረጉት ጥሪ እንደተቋረጠ ወይም እንዳልደረሰ መመዝገብ ይችላሉ፤›› ተብሏል፡፡
Posted on: Mon, 28 Apr 2014 03:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015