Ethiopia: Billion Br Construction of Additional 40/60 Houses - TopicsExpress



          

Ethiopia: Billion Br Construction of Additional 40/60 Houses Commenced | See at .... diretu.be/754863 |በተጨማሪ 1 ቢሊዮን ብር የ40/ 60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ነው ተባለ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች እተገነቡ ከሚገኙት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በ1 ቢሊዮን ብር ወጪ በአያት አካባቢ በሚገኝ 49 ሄክታር መሬት ላይ የ6561 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ እንደሚገኙ የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የአያቱ የ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክትም በአዲስ አበባ ከተማ ዘጠነኛው የ40/60 የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል፡፡ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎቸ እየተገነቡ ከሚገኙት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የልደታው ሳይት 45.4 በመቶውን በማጠናቀቅ ፈጣኑ ፕረጀክትም ነው ተብሏል፡፡ በ40/60 ፣ በ20/80 እና በ10/90 የቤቶች መርሀ ግብር 860,000 ቤት ፈላጊዎች እንደተመዘገቡም ተጠቁሟል፡፡ አዲሱ የአያት ሳይት 133 ብሎኮች የሚኖሩት ሲሆን ብሎኮቹም ከ7 እስከ 12 ፎቆች ይኖራቸዋልም ተብሏል፡፡
Posted on: Fri, 13 Jun 2014 14:57:10 +0000

Trending Topics



talking

Recently Viewed Topics




© 2015