Ethiopia committed to ‘genuine negotiations with Egypt’: - TopicsExpress



          

Ethiopia committed to ‘genuine negotiations with Egypt’: Ethiopian minister ... See at ... diretu.be/285286 | ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር በግልጽ ለመወያየት ፍቃደኛ ነች አሉ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከግብጽ ጋር ግልጽ ውይይት ለማካሄድ ፍቃደኛ ነች ማለታቸው ተሰማ፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህን ያሉት በየመን የተካሄደውን 5ኛውን የሚንስትሮች ኮምሽን ስብሰባ ባጠናቀቁበት ወቅት ለየመኑ ፕሬዝዳንት አብዱ ረቡ ማንሱር ሃዲ ነበር፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ አክለውም የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ለምታደርገው ጉዞ ዋንኛው መሰረትና ግብጽንም ጨምሮ ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ሁለንተናዊ እድገት የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የግብጽ ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም መህሌብ “ኢትዮጵያ ግድቡን የመገንባት ሙሉ መብት አላት ግብጽም የውሃ ፍጆታዋ ሊጠበቅላት ይገባል” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ See at ... diretu.be/285286
Posted on: Sun, 18 May 2014 07:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015