Ethiopia launches direct route to Juba | Read More at - TopicsExpress



          

Ethiopia launches direct route to Juba | Read More at ....goo.gl/H9S2X9 | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኡጋንዳ ኢንቴቤ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ የቀጥታ በረራ ጀመረ፡፡ ከኢንቴቤ ከተማ ወደ ጁባ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት የቀጥታ በረራ መጀመራችን የየሀገራቱ የንግድ ሰዎች በቀላሉ እቃዎችን እንዲያመላልሱ ይረዳቸዋል ሲሉ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጀር አበበ አንጌሳ ተናግረዋል፡፡ ይህም ማለት የኡጋንዳና የደቡብ ሱዳን ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን የኤክስፖርት ልውውጥ ማድረግ ከቻሉ በእጅጉ እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢንቴቤ ወደ ጁባ ለሚያደርገው የቀጥታ በራራ 240 ሰዎችን መያዝ የሚችል ቦይንግ B767 አውሮፕላን ያዘጋጀ መሆኑን ማኔጀሩ ተናግረዋል፡፡ ወደ ጁባ በሚደረገው በረራ 400 የአሜሪካን ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን ከ 1 ሰዓት ያነሰ የበረራ ጊዜ ይወስዳል፡፡
Posted on: Mon, 11 Aug 2014 14:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015