Exactly የዛሬ ኣንድ ኣመት (June 25) Jawar Mohammed, - TopicsExpress



          

Exactly የዛሬ ኣንድ ኣመት (June 25) Jawar Mohammed, The Stream በተባለው የAl Jazeera English ፕሮግራም ላይ Mohammed Ademoና ኣንድ ሌላ ብዙም እራሱን መግለጽ ካልቻለ ፓናሊስት ጋር ቀርቦ defining ሊባል የሚችል ክርክር ኣደረገ። በርግጥም ጃዋርና መሃመድ ኣደሞ በዝግጅቱ ላይ የብዙውን ሰው ቀልብ የሳቡ ሃሳቦችንና ትንታኔዎችን ኣቅርበው ነበር። በዚሁ ወይይት በ18ኛው ደቂቃ ላይ (ፕሮግራሙ ፖስት ሾው ማጠናቀቂያውን ጨምሮ የ34 ደቂቃ ከ24 ሰከንዶች ርዝመት ነበረው) መልክ-ኣልቦ የሆነችው እንግሊዛዊቷ ጋዜጠኛ ፌሚ ኦኪ ጃዋርን ኣንድ ከባድ ጥያቄ በመጠየቅ ኣጣብቂኝ ውስጥ ከተተችው። በነገራችን ላይ ሚስ ኦኪ ከ500 በላይ ቋንቋዎች ከሚነገሩባት ናይጄሪያ ከመጡ ቤተሰቦች የተወለደች እንግሊዛዊት በመሆኗ በኣፍሪካ ማህበረ-ፖለቲካዊ ተዋስኦ (socio-political discourse) ውስጥ የብሄሮች ከዚያም ዝቅ ሲል የጎሳዎች ጉዳይ ያለውን ትልቅ ትጽዕኖ ጠንቅቃ ስለምታውቅ ይመስለኛል ያንን ጥያቄ መጠየቋ። የሆነ ሆኖ ..are you Oromo or Ethiopia first? የሚል ጃዋርን ኣጣብቂኝ ውስጥ የከተተችበትን ጥያቄ ውይይቱ በተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ ላይ ጠየቀችው። ከባድ ኣጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ የተገነዘበ የሚመስለው ጃውርም፤ ላንዲት ኣፍታ ኣሰብ ኣደረገና I am Oromo first ብሎ በመመለስ Ethiopia is imposed on me በሚል ጉዳዩን ሰፋ ባለ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ትንታኔ ማስረዳት ቀጠለ። በነገራችን ላይ በወቅቱ ጥያቄውን የተጠየኩት እኔ ብሆን ኖሮ ቢያንስ በዚያ ፍጥነት ጃዋር ያለውን ማለት የምችል ኣይመስለኝም። I mean, plz escape me on this ልል ሁሉ እችል ይሆናል ሲመስለኝ...ሎል!! እናም ይህች ንግግር ምናልባትም ተናጋሪውን ጃዋር ጭምሮ ብዙዎቻችን ባልገመትነው ሁኔታና መንገድ ነጥራ በመውጣት ባለፈው ኣንድ ኣመት ውስጥ ብዙ ትጽዕኖ ፈጠረች። ተከትሎም ብዙ ታሪካዊ ነገሮች እንዲከሰቱ ምክኒያት ሆነች። የኦሮሞዎችን ኣንድነትም ኣጠናከረች። ደስ የሚለው ነገር በcharacter assassinationና የሴራ ትንትና (conspiracy theory) ጎጂ ባህል በተተበተበውና በከባባድ (ምጡቅ) ሊህቃን የሚመራው የጠቅላይ ኣግላይ ቀኝ መስመር ትዋስኦ (right wing discourse) ቡድን ይህንኑ የOromo First ንግግሩን ተከትሎ ጃዋር መሃመድ ላይ ያወጁት ጦርነት ከthreat ወደ opportunity ተቀይሮ ለጃዋር ብቻ ሳይሆን ለጥቅላላው የኦሮሞ ማህበረሰብ ትልቅ ትርጉም ያለው ስራ እንዲሰራ ምክኒያት ሆነ። Much love and respect to all the the panelists and participants of that defining discussion. Thank you all! https://youtube/watch?v=idvJozrs284
Posted on: Wed, 25 Jun 2014 20:26:30 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015