FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ] ከፍትህ ሬዲዮ 30ኛ - TopicsExpress



          

FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ] ከፍትህ ሬዲዮ 30ኛ ፕሮግራም ላይ ከቀረቡት ዜናዎች የተወሰደ የአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በረመዳኑም የሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ ለማቀዛቀዝ ቃላቸውን አደሱ ፡፡ ህገ ወጡ መጅሊስ እስከዛሬ ተቃውሞውን አፍነውልኛል ያላቸውን መንግስታዊ አካሎች ሁሉ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ (ሽልማት የተበረከታላቸው አካላት ከታች ተካቷል) ረቡዕ ሰኔ 262005 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዐት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል አዳራሽ በተደረገው በዚህ ስብሰባ የአዲስ አበባ ህገወጡ መጅሊስ ሰብሳቢ ዶክተር አህመድ ሰፊና አሰልቺ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም የሙስሊሙን ተቃውሞ ለማቀዛቀዝ ይረዳ ዘንድ ለደህንነቶች እና ለፖሊስ አባላት ያወጡትን የአበል ክፍያ ፣ ለአህባሽ አቀንቃኞች እና መሰል አይነት ስልጠናዎች እንዲሁም ለሌሎች ተያያዝ ለሆኑ ጉዳዮች ወጪ ያደረጉትን ገንዘብ ከመንግስት እንደተበደሩና ብድራቸውን እንደከፈሉ ፣ በዱቤ የተገዙትም መኪኖች ክፍያቸው እንደተጠናቀቀ ፣ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ እንዳቀዛቀዙ ፣ በታሰሩት ህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ለመንግስት የሚችሉትን ያህል የሀሰት ምስክር እንዳቀረቡና ሌሎች መሰል አሰልቺ ጉዳዮች ላይ ሪፖርት እንደነበር የፍትህ የውስጥ ምንጮች በቦታው በመገኘት ዘግበዋል ፡፡ በእለቱ ከሪፖርቱ በተጨማሪ የሽልማት ስነስርዐት የነበረ ሲሆን ፣ ህገ ወጡና መንግስታዊው መጅሊስ የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት እንቅስቃሴ አፍነውልኛል እንዲሁም አቀዛቅዘውልኛል ያላቸውን የመንግስት አካላት ሁሉ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት አበርክቷል ፡፡ በስብሰባው መካከል እና መጨረሻ ላይ ንግግሮች የተደረጉ ሲሆን ዶክተር አህመድ እና የአንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጡሃ ሙስሊሙን እየገደሉ እና እያሰሩ ያሉትን የመንግስት አካላት አላህ እንዲያቆያቸው ዱዐ አድርገዋል፡፡ ሁለቱም ሰዎች “ መንግስታችንን አላህ ያቆይልን ፣ አክራሪዎችን አላህ ያጥፋልን ” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ በተለይ ዶክተር አህመድ በንግግሩ ላይ “ የመንግስት አካላት እና የመጅሊስ አባላት የሆናችሁ ሁሉ አሁንም የአክራሪዎችን እንቅስቃሴ በማቀዛቀዙ ሂደት ላይ እስከመጨረሻው ማገዝ አለባችሁ ”ያለ ሲሆን በአዳራሹ የተገኙትን ተሰብሳቢዎች በጠቅላላ እጃቸውን ወደላይ እንዲያነሱ በማድረግ በረመዳን ላይም የሙስሊሙ ተቃውሞን የማቀዛቀዝ ስራቸውን እንዳያቋርጡ ቃል አስገብቷቸዋል ፡፡ አቶ ኩማ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር እንደተጠበቀው ዶክተር አህመድን ያሞካሹ ሲሆን በንግግራቸው መካከልም “ መንግስትና የአዲስ አበባ መጅሊስ የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት እንቅስቃሴ እንዳቀዛቀዙ ገልፀው አሁንም ቢሆን በመጪው ረመዳን ለሚደረገው ተቃውሞ እዚህ ውስጥ ያላችሁ ሁሉ የማቀዛቀዝ ስራ ላይ ከበፊቱ በበለጠ መስራት ይጠበቅባችኋል ” ብለዋል ፡፡ በመጨረሻ ንግግር እንዲያደርግ የተጋበዘው ደግሞ የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ፕሬዚደንት አቶ ኪያር ሲሆን ፣ የአቶ ኪያር ንግግር በቦታው የነበሩትን የብዙዎችን ሙስሊሞች ቀልብ የገዛ እንደነበር የፍትህ የውስጥ ምንጮች ዘግበዋል፡፡ አቶ ኪያር እንዳለው “ እኔ እንደ ዶክተር አህመድ ብዙ ለመናገር አልተዘጋጀሁም ” በማለት ዶክተሩን በነገር ወረፍ ያደረገ ሲሆን በመቀጠል “ እኔ ያለችኝ መልእክት አጠር ያለች ነች ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ አንድ ታላቅ እንግዳ ይመጣል ፡፡ እሱም ረመዳን ነው ፡፡ በረመዳን ደግሞ ሙስሊም ለሙስሊም አውፍ ይባባላል ፡፡ በረመዳን አንድነታችንን ማጠናከር ነው ያለብን ” የሚል አስገራሚ መልእክት ማስተላለፉን እና ተክቢርም ማስባሉን የፍትህ ሬዲዮ የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡ ይህ የኪያር ድርጊት ዶክተር አህመድን እና የመንግስት ሰዎችን እንዳላስደሰተም ታውቋል ሲሉ ምንጮች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል፡፡ የህገ ወጡ አዲስ አበባ መጅሊስ የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል እንዲቀዛቀዝ እገዛ አድርገዋል ብሎ ሽልማት ካበረከተላቸው ተቋማት እና ግለሰቦች በማከል በጥቂቱ 0) ለአዲስ አበባ ደህንነት ቢሮ 1) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2) ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 3) ለአቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም (የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ) 4) ለኮማንደር መኮንን አሻግሬ (የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ) 5) ለአዲስ አበባ ኢሃዴግ ፅህፈት ቤት 6) ለዳእዋ እና ፈትዋ ዘርፍ 7) ለአዲስ አበባ መሬትና ይዞታ ፅህፈት ቤት ለኢትዮፕያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዝን ድርጅት 9) ለሬዲዮ ፋና 10) ለአንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጡሃ ሃሩን 11) ለሀጅ ሰይድ ግዛው (የቀድሞው መጅሊስ) 12) ለሸህ ኢዘዲን (የድሮው መጅሊስ ፀሃፊ) 13) ለአቶ በቀለ ጉጉታ 14) ለሲሳይ ሀብቴ 15) ለአቶ ስዩም 16) ለአቶ ገዛሃኝ ገዙ 17) ለሙሉጌታ አሰፋ 18) ለመስታወት ፍቃዱ 19) ለአቶ ሰለሞን 20) ለአብድረዛቅ ኢብራሂም 21) ለአቶ ብርሃኑ 22) ለወይዘሮ አልማዝ 23) ለመለሰ ካሳዬ 24) ለአቶ ሙሉጌታ አደታ 25) ለጌታሁን አበራ 26) ለሰለሞን በቀለ 27) ለፍቅር ተስፋዬ 28) ለወይዘሮ አበባ 29) ለወይዘሮ ፀሀይ ረጋሳ 30) ለአቶ አሸናፊ ሞላ 31) ለሰባቱ ሀይማኖቶች ጉባኤ ተቋማት ሰብሳቢ
Posted on: Wed, 10 Jul 2013 08:51:39 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015