Fith radio 74 for Mobile: goo.gl/OBjfxq Fith radio 74 for PC: - TopicsExpress



          

Fith radio 74 for Mobile: goo.gl/OBjfxq Fith radio 74 for PC: goo.gl/pUV8nU በሙስሊሙ ማህበረሰብ ያልተቋረጠ ብርቱ ትግል ህገ ወጡ መጅሊስ እንደተፍረከረከ የኢትዮፕያ ህዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢህአዴግ ) የፖለቲካ ክንፍ አመነ ፡፡ እንደ ፓርቲው የፖለቲካ ክንፍ እምነት ከሆነ መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄዎች መልሻለሁ ለማለት ያህል እራሱ መርጦ የሾማቸው የህገ ወጡ መጅሊስ አመራሮች ከሚጠበቅባቸው በታች ሆነው በመገኘታቸው መንግስት ከሙስሊሙ አንፃር ሊተገብራቸው የነበሩ እቅዶች ሁሉ አብዛኞቹ ሲከሽፉ ሌሎቹ ደግሞ የለብ ለብ ያህል ተሰርተው ውጤት አልባ እንደሆኑ አስምሮበታል ፡፡ በተለይ ደግሞ የሙስሊሙ ተቃውሞው ሳይቆም ምርጫ መቃረቡ ፓርቲውን ተጨማሪ ስጋት ላይ እንደጣለው የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ሊሆን የቻለው መጅሊሱ ጠንካራ ባለመሆኑና ሁሉን ነገር ከመንግስት የሚጠብቅ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተጠቁሟል ፡፡ በተለይ ደግሞ የክፍለ ከተማና የክልል መጅሊሶች አሉ ከመባል ውጪ ወርደው ህዝቡ ጋር የመስራት ሞራልም ሆነ ፍላጎት እንደሌላቸው የተገመገመ ሲሆን ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት አክራሪዎቹ በፈጠሩባቸው የስነ ልቦና ጉዳት እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሁሉንም አይነት ተግዳሮቶች ተቋቁሞ ትግሉን አለማቆሙ ለህዝቡ ብርታት የሆነው ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ መጅሊስ አባላት መፍረክረክና የመንግስት እቅዶች በአጥጋቢ ሁኔታ እንዳይፈፀሙ እንቅፋት እንደሆኑ ተነግሯል ፡፡ ህገ ወጡ መጅሊስ ተመርጧል ተብሎ በይፋ ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ የኢህአዴግ ትልቁ ግብ ተቃውሞው ቁሞ ህዝቡ በመጅሊሱ ፍላጎት እንዲመራና በሂደትም ተቃውሞውን ረስቶ ወደየራሱ ኑሮ እንዲመለስ ቢሆንም የተመረጡት የመጅሊስ አመራሮች በራሳቸው የማይተማመኑና ሁሉን ነገር ከመንግስት ጠባቂዎች በመሆናቸው መጅሊሱ የመንግስት ተለጣፊ እንደሆነ በአክሪዎች የተሰራው ፕሮፖጋንዳ ኢማላውን እንዳገኘ የፓርቲው ክንፍ አምኗል ፡፡ በዚህ ምክንያት የመጅሊሱ አመራሮች በተለይም ፈፃሚ አካላት የህዝብ እምነት ማግኘት ባለመቻላቸው ኮር የሆኑ ግቦች ሁሉ ውጤት አልባ እንደሆኑ ታውቋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሊፈፀሙ የታሰቡ እቅዶች ሁሉ ቅድመ እና ድህረ አፈፃፀም ላይ እያሉ በመጅሊስ አባላት አማካኝነት ለአክራሪዎች እንዲደርሱ መደረጋቸው ታማኝ የመጅሊሱ ተመራጮች ላይ ድንጋጤ መፍጠራቸው የተገመገመ ሲሆን ለአክራሪዎቹ ደግሞ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ሞራል እንደሰጣቸው ታምኗል ፡፡ መስጂዶችን እና መድረሳዎችን የመቆጣጠር እቅዱ በአጥጋቢ ሁኔታ የተሳካ ቢሆንም ይህን ያደረገው መጅሊሱ ሳይሆን ፍትህ ቢሮዎች መሆናቸው በአክሪዎቹ በሰፊው በመዘገቡ መንግስትን ለሌላ ከባድ ፕሮፖጋንዳ ሽንፈት ውስጥ እንደከተተው እና ህዝቡም በዚያ ስሜት እንዲቀበለው መደረጉ በድክመትነት ተነስተዋል ሲሉ የውስጥ ምንጮች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል ፡፡
Posted on: Sat, 10 May 2014 18:13:18 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015