Genene Mekuria Libro እኛ የሚያስፈልገን - TopicsExpress



          

Genene Mekuria Libro እኛ የሚያስፈልገን የሚነጥቅ ሳይሆን የማይነጠቅ ነው፡፡ በቻን ውድድር ሩዋንዳን ገጠምን፡፡ አዲስ አበባ ላይ ሩዋንዳን ብዙ ጊዜ አይቼዋለሁ፡፡ እንደዚህ የደከመ ሩዋዳ ግን አይቼ አላውቅም፡፡ ወደኛ ጎል መምጣት ከፈለገ በቀላሉ ከተፍ ይላል፡፡ በነገራችን ላይ በአንዳንድ ሚዲያዎች ላይ ኮከብ ተብሎ የተደነቀው ጀማል ጣሰው ነው፡፡ ጀማል በረኛችን ነው፡፡ ከሩዋንዳ ጋር በረኛችን ምርጥ ነው ከተባለ ቡድናችን በጣም ተጠቅቷል፡፡ ይህ ደግሞ ቡድናችን ምን ያህል እንደወደቀ የሚያሳይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ትልልቆቹ እነ ናይጄሪያ ግብፅ እንኳን ወጥተው አይጫኑንም፡፡ ሩዋንዳ በረኛችንን ካስመሰገነ አጨናንቆናል ማለት ነው፡፡ ይህ እኮ የሚያሳየው ኳስ ቶሎ ቶሎ ለነሱ እየሰጠን እንዲያጠቁን እያደረግን ነው፡፡ ቴክኒካል ተጫዋች ይዘን ኳስን ተቆጣጥሮ በኛ ቡድን ስር ማድረግ የሚችል ሰው ስለሌለን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአሰልጣኙ ችግር ነው፡፡ አሰልጣኙ ከማይነጥቅ ይልቅ የሚነጥቅ ተጫዋች ስለሚያስገባ ነው፡፡ የሚነጥቅ ተጫዋች ማለት ነጥቆ ለባላጋራ የሚሰጥ ነው፡፡ የማይነጠቅ ተጫዋች ማለት ኳስን ይዞ ለራሱ ጓደኛ የሚሰጥና በአግባቡ ጎል ጋር የሚያደርስ ነው፡፡ በቡድናችን ኳስ የሚበላሸው የአሰልጣኙና የአሰለጣጠን ችግር ነው፡፡ ‹‹ንጠቅ›› እና ‹‹ተጫወት›› ትልቅ ልዩነት አላቸው፡፡ ለ ‹‹ንጠቅ›› ከነጠቀ በኋላ ምንም ተሳትፎ የለውም፡፡ በነገራችን ላይ ነጣቂ ተጫዋች ከነጠቀ በኋላ ቡድኑ ሲጫወት መሳተፍ አይችልም፡፡ በዚህ የተነሳ ቡድናችን ሲያጠቃ ብዙ ጎዶሎ ተጫዋች ይበዛል ምክንያቱም ነጣቂዎች ስራቸው ኳስ ስንነጠቅ መንጠቅ ብቻ ነው፡፡ የሚጫወት ግን ኳስ ሲይዝ ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰው ሲፈልግ ነጣቂዎቹ አያግዙትም፡፡ አጋዥ ስለሌለው ወደ ግል ነገር ይገባና ይነጠቃል፡፡ በዚህ የተነሳ ከነጣቂዎቹም ከተጫዋቾቹም ሳንሆን እንቀራለን፡፡ ከተጫዋቾቹ ሳንሆን የቀረነው ነጣቂ ስለሚበዛ መጫወት ስለማንችል ነው፡፡ ነጣቂ ያበዛው ደግሞ አሰልጣኙ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የሚያስፈልገን የሚነጥቅ ሳይሆን የማይነጠቅ ነው፡፡
Posted on: Wed, 17 Jul 2013 04:39:13 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015