Horrific Traffic Accident in Addis Kills Eight Wounding forty Six - TopicsExpress



          

Horrific Traffic Accident in Addis Kills Eight Wounding forty Six .... see More At ..... . diretu.be/454294| አሁን አሁን በየቀኑ እየሰማን ካለነው አስከፊ የመኪና አደጋዎች አንዱ ቢሆንም በዛሬው ዕለተ እሁድ መጋቢት 14 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ዘነበወርቅ ድልድይ ላይ የደረሰው የመኪና አደጋ እጅግ አስከፊ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ዛሬ ማለዳ ላይ 12፡40 አካባቢ ከካራ ወደ መርካቶ ይሄድ የነበረ ኮድ 3 - 7366 የሆነ አንበሳ የከተማ አውቶብስ 113 ተሳፋሪዎችን እንደጫነ የመንገድ መከለያ ኮንክሪቱን ጥሶ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ዘነበወርቅ ድልድይ ውስጥ ገብቷል፡፡ በአደጋው 8 ሰዎች ሲሞቱ 46ቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ አደጋውን አስመልክቶ መረጃውን ያቀበሉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን የኮምንኬሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ከአደጋው ሰለባዎች አብዛኞቹ ወለቴ አካባቢ በሽመና የሚተዳደሩና ነጠላ እና መሰል የሽመና ውጤቶቻቸውን ይዘው ወደ ሽሮሜዳ ገበያ ለመሄድ አውቶብሱን የተሳፈሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በአደጋው የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ተጎጂዎች በጳውሎስና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ የአውቶብሱ ሾፌር ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበት ተርፏል፡፡ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ ነው፡፡ ሙሉ የቪድዮ ሪፖርቱን ይከታተሉ ..... diretu.be/454294
Posted on: Sun, 23 Mar 2014 14:44:42 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015