Imported telecom equipment create disarray .... See at ... - TopicsExpress



          

Imported telecom equipment create disarray .... See at ... diretu.be/952565 | ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ሞጆ ደረቅ ወደብን በጎበኙ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 13 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ዕቃዎች በሕገወጥ መንገድ አስገብቷል የተባለው የቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ፣ ዕቃዎቹን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ አቀረበ ተባለ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ የተመሠረበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሞጆ ደረቅ ወደብን ጎብኝተው እንደነበረ እና በጉበኝታቸው ወቅት ሁዋዌ ያስገባቸው 24 ኮንቴይነሮች መውጣታቸውን ሲጠይቁ፣ ኮንቴይነሮቹ እንዳልወጡ ከደረቅ ወደቡ ባለሥልጣናት እንደተገለጸላቸው ያመለከተው የሪፖርተር ዘገባ ምክንያቱን ማንም እናዳልመለሰላቸው እና ‹‹ሁዋዌ ዕቃዎቹን አልፈለጋቸውም ማለት ነው?›› የሚል ጥያቄ ጠይቀው እንደነበረ ጠቁሟል፡፡ ከዓመት በላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ የተቀመጡትን 23 ኮንቴይነሮችና በኮሜት ተርሚናል ውስጥ የተቀመጠውን አንድ ኮንቴይነር ለማስወጣት ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሁዋዌ ጥያቄ ማቅረቡን ምንጮቹነረ ጠቅሶ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የሞጆ ደረቅ ወደብ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ምሕረትአብ ተክሉ ሁዋዌ ሞጆ ደረቅ ወደብ የሚገኙትን ኮንቴይነሮች ወደ ጂቡቲ ለመመለስ ጥያቄ ማቅረቡን መናገራቸውም ተገልጿል፡፡ ዕቃዎቹ ከቻይና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. በመርከብ ተጭነው ከአንድ ወር በኋላ ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው ተጠቁሟል፡፡ ለዝርዝሩ ....diretu.be/952565
Posted on: Sun, 18 May 2014 11:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015