Justice ministers and attorney generals of African Union (AU) - TopicsExpress



          

Justice ministers and attorney generals of African Union (AU) member countries are scheduled to meet in Addis Ababa, Ethiopia on May 15 and16, to consider a draft protocol to expand the authority of the African Court on Justice and Human Rights | በትላንትናው ዕለት የወጣ አንድ መረጃ እንደሚጠቁመው የፊታችን ሐሙስና አርብ (ግንቦት 7 እና 8 2006 ዓ.ም) የአፍሪካ ፍርድ ቤት ለፍትሕና ሰብዓዊ መብት (African Court on Justice and Human Rights) የተባለውን አህጉራዊውን ተቋም ስልጣን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ ፕሮቶኮል ላይ ለመምከር የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የፍትሕ ሚንስትሮችና ጠቅላይ አቃቢያነ ህግ በአዲስ አበባ ይሰበሰባሉ፡፡ ይሻሻላል የተባለው የፍርድ ቤቱ ሥልጣን የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጦር ወንጀሎችንና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የመዳኘት ሥልጣንን እንደሚመለከት ተጠቁሟል፡፡ ረቂቅ ሕጉ ከላይ በተዘረዘሩት ወንጀሎች የሐገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዳይጠየቁ የማድረግ ኃሳብ መያዙ ፍርድ ቤቱ ወንጀሎቹን ለመዳኘት ያለውን የሞራልና የህግ ብቃት ይሸረሽረዋል ተብሏል፡፡ ሚዲያ ፋውንዴሽን ፎር ዌስት አፍሪካ የተባለው ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሱሌይማን ብሬይማን፣ “የመንግስታት መሪዎችንና ከፍተኛ ባለሥልጣናትን በአፍሪካ ፍርድ ቤት እንዳይጠየቁ የማድረጉ እንቅስቃሴ ስልጣን ያላቸውን ከሕግ በላይ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ነው” ይላሉ፡፡ የጉዳዩ ታዛቢዎች እንደሚሉት የአፍሪካ ሀገራት የፍርድ ቤቱን ሕግ ለማሻሻል መንቀሳቀስ የጀመሩት ዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court - ICC) በኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩታ ላይ ክስ መመስረቱን አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መቃወማቸውን ተከትሎ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ዝርዝር...diretu.be/683669
Posted on: Tue, 13 May 2014 13:45:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015