Multidimensional Poverty Index (MPI) የተባለውና - TopicsExpress



          

Multidimensional Poverty Index (MPI) የተባለውና የዓለማችንን 108 በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የድህነት ደረጃ የፈተሸው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ጥናት ኢትዮጵያን ከ108ቱ ሀገራት ከኒጀር ብቻ በልጣ ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡ ደረጃው በትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥኑ 10 መስፈርቶች ሲኖሩት ከ10ሩ መስፈርቶች አንድ ሦስተኛውን እንኳ ያላገኘን ደረጃው ዘርፈብዙ ደሃ (Multi-dimensionally poor)ሲለው፣ ከመስፈርቱ ዝርዝር ውስጥ አንድ ሦስተኛው ያህል የተሟላለትን ደግሞ ለኑሮ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) ይለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ 87.3% ያህሉ ዘርፈብዙ ደሃ በሚለው ክልል ውስጥ ሲገኝ 58.1%ቱ ደግሞ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) በሚለው ክልል ውስጥ እንደሚገኝ የጥናት ውጤቱ ያስረዳል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉላቸው (Destitute) ዜጎቿን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ጥሩ ውጤት ብታስመዘግብም ኢትዮጵያ አሁንም የ76 ሚሊየን ዘርፈብዙ ደሃ ህዝብ ሀገር ናት ይላል የጥናት ውጤቱ፡፡ ይህም ቁጥር በዓለማችን ካሉ መሰል በርካታ እጅግ ደሀ ሕዝብ ከያዙ ሀገራት ማለትም ከህንድ፣ ቻይና፣ ባንግላዴሽ እና ፓኪስታን በመቀጠል ኢትዮጵያ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የደረጃው ዝርዝር የገጠሪቱን ኢትዮጵያ አስመልክቶ 96.3% የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ ሲገልጽ በአንጻሩ ከከተማ ነዋሪው 46.4 %ቱ በድህነት ውስጥ እንዳለ ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚስተዋለውን የድህነት ደረጃ አስመልክቶም በሶማሊያ 93% በኦሮሚያ 91.2% በአፋር 90.9% በትግራይ 85.4 % በአማራ 90.1 % ህዝብ በድህነት ውስጥ እንዳለ ይገልጻል፡፡ ከተሞችንም በተመለከተ አዲስ አበባ ከሌሎች ከተሞች ይልቅ አነስተኛ ደሃ (20%)ያለባት ስትሆን ድሬዳዋና ሐረር ደግሞ አነስተኛ ደሃ በመያዝ በ54.9% እና በ57.9% ይከተላሉ ========||=====| Ethiopia ranks second poorest country in the world - Oxford University Study According to The Global Multidimensional Poverty Index (MPI), published by Oxford University, Ethiopia ranks the second poorest country in the world just ahead of Niger. The study is based on analysis of acute poverty in 108 developing countries around the world. Despite making progress at reducing the percentage of destitute people, Ethiopia is still home to more than 76 million poor people, the fifth largest number in the world after India, China, Bangladesh and Pakistan. India has the worlds largest number of poor people at more than 647 million. 87.3% of Ethiopians are classified as MPI poor, while 58.1% are considered destitute. A person is identified as multidimensionally poor (or MPI poor) if they are deprived in at least one third of the weighted MPI indicators. The destitute are deprived in at least one-third of the same weighted indicators, The Global MPI uses 10 indicators to measure poverty in three dimensions: education, health and living standards. In rural Ethiopia 96.3% are poor while in the urban area the percentage of poverty is 46.4%. Comparing the poverty rate by regions, Somali region has the highest poverty rate at 93% followed by Oromiya (91.2%) and Afar (90.9%). Amhara region has 90.1% poverty rate while Tigray has 85.4%. Addis Ababa has the smallest percentage of poverty at 20% followed by Dire Dawa at 54.9% and Harar (57.9%)
Posted on: Thu, 19 Jun 2014 21:00:31 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015