Our response will be decisive: Egypt tells Ethiopia on Nile - TopicsExpress



          

Our response will be decisive: Egypt tells Ethiopia on Nile dispute - የግብጽ ድንፋታ…. እና የኢትዮጵያ እርጋታ የግብጽ የተለያዩ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለችው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችን መሰንዘር የዘወትር ተግባራቸው አድርገው ይዘውታል። በቅርቡም የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …… ታህሪር ሳተላይት ቻናል ከተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ከፍተኛ የማስፈራራት እና የዛቻ ንግግር ሲያደርጉ ተሰምተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የግብጽን ህዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከማስከበር ሃገራቸው ወደ ኋላ እንደማትል እና ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የማትችል ከሆነ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። «ከማንኛውም አደጋ ራሳችንን እንጠብቃለን፣ ከኢትዮጵያም ጋር ድርድር እናደርጋለን ነገር ግን ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው ድርድር ውጤቱ ካላማረ ለሚፈጠረው ቀውስ ኢትዮጵያ ሃላፊነቱን ትውስዳለች ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን እነዚህ እና የመሳሰሉ የማስፈራሪያ እና የዛቻ ንግግሮች የትም እንደመያደርሱ በተላያዩ መንገዶች ትዕግስት የተሞላበት አስተያየት ሲሰጥ ነው የሚደመጠው። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲም በጉዳዩ ላይ ለድሬቲዩብ የሰጡት አስተያየትም ከዚህ የተለየ አይደለም። በመጀመሪያ ይላሉ አምባሳደር ዲና « በመጀመሪያ ኢትዮጵያ በግብጽም ሆነ በታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ላይ አደጋ የሚያመጣ ምንም አይነት እቅድ የላትም፤ ይህም በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው»። ቃል አቀባዩ የግብጽ ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እስካልደፈሩ ድረስ የፈለጉትን የማለት መብት እንዳላቸውም ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግብጾች እራሳቸው ከሶስትዮሹ የቴክኒክ ኮሚቴ ድርድር ወጥተው በተለያዩ የአረብ ሃገራት አደራዳሪነት አዲስ ውይት ይጀመር ይላሉ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሶስትዮሹ የቴክኒክ ኮሚቴ ድርድር ውጪ ማንኛውንም አይነት አደራዳሪም ሆነ ድርድር እንደማትቀበል ነው አምባሳደሩ የገለጹልን። የግብጽ ባለስልጣናት በተለያዩ ግዚያት የሚናገሯቸው ንግግሮች «ህገወጥ ናቸው» ያሉት አምባሳደሩ አሁን እየተከተሉት ያለው አቋም የግብጽን ህዝብ የሚጎዳ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ይህንኑ የሚያደርጉበት የራሳቸው ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች አሏቸው ብለዋል። ተጀምሮ ከነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ምንም እንዃ ግብጽ እራሷን ብታገልም ዞሮ ዞሮ ድርድሩ ለግብጽ ህዝብ የሚጠቅም በመሆኑ የግብጽ መንግስት ወደ ድርድሩ ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል።
Posted on: Sun, 09 Mar 2014 21:35:22 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015