Security First | ጥንቃቄ ይቅደም! በኢትዮጵያ - TopicsExpress



          

Security First | ጥንቃቄ ይቅደም! በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ብቸኛው በዲጂታል ደህንነትና በኢንተርኔት ነፃነት ላይ የሚያወራ ጦማር። The First And The Only Blog About Digital Security And Internet Freedom In Ethiopia! Wednesday, 26 March 2014 “በስልክ የምናወራውን ሁሉ ያውቃሉ” መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂውማን ራይትስ ዎች’ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን እንደሚሰልል መጋቢት 16 ባወጣው ሪፖርቱ ገለፀ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ 145 ገፅ በሚደርሰውና “THEY KNOW EVERYTHING WE DO: Telecom and InternetSurveillance in Ethiopia” የሚል ርእስ በሰጠው ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት የቻይናና የአውሮፓ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያና በባህር ማዶ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎችን የስልክና ኢንተርኔት እንቅስቃሴ እንደሚሰለል ገልጿል። ስለ ሪፖርቱ ኤ.ኤፍ.ፒ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሚንስተር አቶ ሬድዋን ሁሴን “የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማጥፋት ከሚደረጉ ዘመቻዎች አንዱ መሆኑን ስለምናውቅ ለሪፖርቱ መልስ መስጠት አስፈለጊ አይደለም” በማለት ሪፖርቱን ቢያጣጥሉም ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ የመንግስት የስለላ ክንፍ የሆነው የመረጀና ደህንነት ኤጀንሲ INSA የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ በለቀቀው ሪፖርት ተደናግጠው ‘ውስጣችን መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ አለ’ እስከማለት እንደደረሱ ምንጮቻችን ገልፀውልናል። ሂውማን ራይትስ ዎች በርፖርቱ አያይዞ የደህንነቶች ሀይሎች የተቀዱ የስልክ ልውውጦችን በፈለጉት ጌዜ የሚያዳምጡ ሲሆን ካለምንም ህጋዊ ድጋፍ የዜጎችን ስልክ ጠልፎ በመቅዳት የተቃውሞ ድምፅን ለማፈን እንደሚጠቀሙበትና በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚገኙ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ኮምፒተሮች ላይ ለስለላ የሚያገለግል ሶፍትዌር (spyware) በመላክ በኦንላይን የሚያደርጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን እንደሚሰልል ርፖርቱ ጠቅሷል። በኢንተርናሽናል ኮምንኬሽን ዩንየን ጥናት መሰረት 23% ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቀሽ ስልክ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ በስለላው ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን መንግስት ትደግፋለች ተበላ የምትወቀሰው ቻይና ሁለት ትላልቅ ካምፓኒዎቿ ዜድቲኢ እና በአሜሪካ መንግሥት የስለላ ሶፍትዌር እና ሃርድዌር ይጠቀማል በሚል ተጠርጥሮ የታገደው ህዋዌ የአገሪቱን የቴሌኮም ማስፋፋት ፕሮጀክት ወስደው እያሰሩ ይገኛሉ። ኢትዮ ቴሌኮም በዜድ.ቲ.ኢ የተሰራ Zsmart የተሰኘ የደንበኞች አገልግሎት መቆጣጠርያ የመረጃ ቋት የሚጠቀም ሲሆን ይህ የመረጃ ቋት (Zsmart database) ሶፍትዌር የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞችን ግላዊ መረጃዎች ማለትም፡ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ብሄርና ደንበኛው ያደረጋቸውን ሙሉ የስልክ ልውውጦች (የደዋዩንና የተቀባዩን) በሙሉ የሚመዘግብ የመረጃ ቋት ሶፍትዌር ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ ለሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እንደተናገረው በመንግስት ደህንነቶች ክትትል ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ሊስት Zsmart የተሰኘው መረጃ ቋቱ ውስጥ ከገባ በኋላ ሶፍትዌሩ አውቶማቲካሊ የግለሰቦቹን የስለክ ጥሪ መቅዳት እንደሚጀምር ተናግሯል። በመንግስት እስር የተፈፀመባቸው ግለሰቦችም በማእከላዊ መርመራ ላይ መርማሪዎቹ ከዚህ ቀደም የደረጓቸውን የስልክ ንግግርች ቀድተው እንደሚያጫውቱላቸው ተናግረዋል። በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ይሰራ የነበረ ግለሰብ ለሂውማን ራይትስ ዎች እንደሰጠው መረጃ መሰረት ከሆነ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞችና መንግስት በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው ድርጅቶች ኦነግ፣ ግንቦት7ና ኦብነግ፤ እንዲሁም አገር ውስጥ ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ የሚንቀሳቀሰው አንድነትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጋለ የመጣው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ ቅርብ የሆኑና ግንኘነት ያላቸው ግለሰቦች በኢትዮጵያ መንግስት የስለላ መረበው ውስጥ ዋነኛ ኢላማ እነደሆኑ ገልጿል። ሂውማን ራይትስ ዎች ያነጋገረቸው ግለሰቦች እንደገለፁለት ከሆነ መንግስት የስልክና የኢሜል መልእክት ለውውጦችን ይጠልፋል ብለው ስለሚያስቡ በስልክና በኢሜል ልውውጠቻቸው ወቅት እራሳቸውን እንደሚያቅቡ (እራሳቸው self-censor እንደሚያደርጉ) ተናግረዋል።
Posted on: Wed, 26 Mar 2014 13:47:14 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015