Standing committee slams CSOA agency for poor performance ... See - TopicsExpress



          

Standing committee slams CSOA agency for poor performance ... See at ... diretu.be/272436 | ፓርላማው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ ሕጉን በአግባቡ እያስፈጸመ አይደለም አለ ‹‹ሕጉን ሙሉ ለሙሉ እናስፈጽም ካልን ሁሉም ድርጅቶች መዘጋት ነበረባቸው›› የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በ2001 ዓ.ም. የፀደቀውን አወዛጋቢውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ማኅበራት አዋጅን እንዲያስፈጽም በአዋጅ የተመሠረተው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ ኤጀንሲ፣ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሕጉን በማስፈጸም ረገድ ድክመት አለበት መባሉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧ፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና የፕሮጀክቶችን በመከታተል ረገድ ያከናወናቸው ተግባሮች ደካማና አመርቂ አይደሉም ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2005 ዓ.ም. የበጀት ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን፣ በኦዲት ሒሳብና ክንዋኔ ሪፖርቱ ከዳሰሳቸው 138 የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ኤጀንሲው ይገኝበታልም ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ኤጀንሲው አሉበት የተባሉትን የማስፈጸም አቅም ችግር ላይ ለማነጋገር የኤጀንሲው ኃላፊዎችና የዋና ኦዲተር መምሪያ ቤት ኃላፊ ባለፈው ረቡዕ በቋሚ ኮሚቴው ተጠርተው እንደነበረ እና የኦዲት ሪፖርቱን በመጥቀስ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተሾመ እሸቱና ሌሎች አባላት የኤጀንሲውን የአፈጻጸም ድክመት በተመለከተ የተለያዩ ነጥቦችን በመንቀስ የኤጀንሲውን ኃላፊዎች በጥያቄ ሲያፋጥጧቸው ማርፈዳቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ሙሉ ዜናውን ያንብቡ ....
Posted on: Sun, 04 May 2014 09:14:34 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015