Sudan’s FM accuses Egypt’s spy agency of aiding Cairo-based - TopicsExpress



          

Sudan’s FM accuses Egypt’s spy agency of aiding Cairo-based rebels ...See at ... diretu.be/374295 | የሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎቼን በገንዘብ ትደግፋለች በሚል ግብጽን ወነጀለ የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ካርቲ የግብጽ የደህንነት ዳይሬክቶሬት መሰረታቸውን በካይሮ ያደረጉ የሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎችን በገንዘብ ይረዳል ሲሉ ከሰዋል፡፡ ‹‹ የግብጽ መንግስት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግሰት ተቃዋሚ የጦር ሃይል አባላቱ መሳሪያ የታጠቁ መሆኑን የዘነጋው ይመስላል ፤ በግብጽ የሚገኙ የሱዳን መንግስት ተቃዋሚ ሃይሎች በግብጽ የደህንነት መስሪያ ቤቶች እና በሃገሪቱ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው ከመሆኑ ባለፈ ስብባዎች እና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርጉም እየተፈቀደላቸው ነው ›› ብለዋል የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ካርቲ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም የሱዳን መንግስት እጅግ በተደጋጋሚ ለግብጽ መንግስት ጉዳዩን ያሳሳበ ቢሆንም በመጨረሻ የግብጽ መንግስት ስለ ግለሰቦቹ መረጃ እንድናቀርብ ጠየቀን ያንንም አደረግን ፤ ግብጾቹ የሚገኙበትን ቦታ ጠየቁን ይህም ይሁን ብለን በየአካባቢዎቹ ያሉትን ሁኔታዎች አስረዳን የግብጽ መንግስት ግን ምላሽ መስጠት አልፈለገም፤ እኛ ማን የት እንዳለ እናውቃለን ነገር ግን የግብጽ መንግስት ከእነሱ ጋር እየተዋዋለ ነው ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት አንድ የሱዳን ዲፕሎማት ‹‹ ሱዳን በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ላይ የመግባት ፍላጎት የላትም የግብጽ ሉአላዊነትንም ታከብራለች ነገር ግን ግብጽ ይህን ማድረግ አልቻለችም›› ብለዋል ፡፡ የግብጽ መንግስት ሱዳን ለታላቁ የኢትዮያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ መስጠቷ እና የግብጽ መንግስት ተሰሚነቱን እና ተጽእኖ ፈጣሪነቱን እንዲያጣ ምክንያት በመሆኑ ከሱዳን መንገስት ጋር ያለው ግንኙነት እየሳሳ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ ለዝርዝሩ ........... diretu.be/374295
Posted on: Fri, 23 May 2014 11:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015