The Patriarch Bans Mahebere Kidusan’s Seminar ...See at ... - TopicsExpress



          

The Patriarch Bans Mahebere Kidusan’s Seminar ...See at ... diretu.be/924476 | ፓትሪያርኩ የማህበረ ቅዱሳንን የጥናት ጉባኤ አገዱ ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ማህበረ ቅዱሳን ስለ ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት አይነት እና ይዘት ትንተና እንዲሁም አያያዝ እና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚያም ጠርቶት የነበረው የግማሽ ቀን ጉባኤ ከፓትሪያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በተጻፈ እና የፓትሪያርኩን ቲተር እና ፊርማ ይዞ በወጣው ደብዳቤ መታገዱን አዲስ ጉዳይ መጽሄት አስነብቧል፡፡ ሴሚናሩ የታገደው ‹‹ በቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተጠሩበት መንገድ ‹ የስልጣን ተዋረድን እና የዕዝ ሰንሰለቱን አልተከተለም › በሚል›› መሆኑን ደብዳቤው እንደሚያመለክት ዘገባው አመልክቷል፡፡ የፓትሪያርኩ ደብዳቤ ‹‹ ጉዳዩን አናውቀውም ፣ ፈጽሞም ፈቃድ አልሰጠንበትም… አሁንም ሆነ ወደ ፊት ከመንበረ ፓትሪያርክ ልዩ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳታገኙ ከቤተክርስቲያን ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች በሙሉ ስብሰባም ሆነ በከፊል ጉባኤ ማድረግ የማትችሉ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን›› ማለቱም ተጠቅሷል፡፡
Posted on: Sat, 03 May 2014 15:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015