U.N. expecting to feed 6.5 million Ethiopians this year See at... - TopicsExpress



          

U.N. expecting to feed 6.5 million Ethiopians this year See at... diretu.be/556953 | የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለ6.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የምግብ ዕርዳታ አቀርባለሁ አለ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከጄኔቭ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በአንበጣ መንጋ፣ በጐረቤት አገር ጦርነትና በዝናብ እጥረት ምክንያት ዕርዳታው ያስፈልጋታል ብሏል፡፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቃል አቀባይ ኤልዛቤት ባይርስ እንዳሉት ከሆነ ‹‹የአንበጣ መንጋ ወረራ በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል እየተከሰተ በመሆኑ ያሳስበናል፡፡ ይህ በአግባቡ ካልተያዘ ለአርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ በጣም አሳሳቢ ነው፤›› በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ ሥርጭቱ ከአማካዩ ጋር ሲነፃፀር ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ቀንሷል ሲሉ ቃል አቀባይዋ አስረድተዋል፡፡ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ዕርዳታ ማግኘት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ከተፈጥሮአዊ ችግር በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የስደተኞች ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ በመጨመሩ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በጀት መዛባቱን ገልጸዋል፡፡ ተጨማሪ አዳዲስ ስደተኞች እየጎረፉ በመሆናቸው ምክንያት የበጀት እጥረት ችግር ስለሚያጋጥም ዕርዳታ ያስፈልጋል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ See at... diretu.be/556953
Posted on: Thu, 15 May 2014 03:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015