US, EU want Egypt, Ethiopia to restart dam talks..See More - TopicsExpress



          

US, EU want Egypt, Ethiopia to restart dam talks..See More Here...diretu.be/462277 | የአሜሪካ እና የአወሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ እና ግብጽ ዳግም ወደ ውይይት እንዲመለሱ እየሸመገሉ ነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ ካይሮ በመመላለስ ኢትዮጵያ ፣ግብጽ እና ሱዳን የጀመሩትን ድርድር እንዲቀጥሉ ደፋ ቀና ማለት ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያን እና ግብጽን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች በታለቁ የኢትዮጵያ የህደሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል ተጀምሮ የነበረውን የሶስትዮሽ መድረክ እንደገና እንዲጀመር በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ሆነው ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ዲፕሎማቶቹ ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም መስፈን እገዛ ማድረግ ፍጎታቸው እንደሆነ መናገራቸውም ተመልክቷል፡፡ በኢትዮጵያ በግብጽ እና በሱዳን መካከል እ.ኤ.አ በ2011 ተጀምሮ የነበረው እና ግድቡ በታቸኛው የወንዙ ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያደርሰው አሉታው ተጽእኖ መኖሩን እና አለመኖሩን የሚያጠናው የሶስትዮሽ ኮሚቴ ግብጽ ‹‹ግድቡ ታሪካዊ የውሃ ድርሻዬን ያሳጣኛል ›› በሚሉ እና በሌሎች ምክንያቶች እራሳን በማግለሏ መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የውሃ ጉዳዮች ልዩ አስተባባሪ አሮን ሳልስበርግ እና የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አሌክሳንደር ሮንዶስ በግብጽ ከከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ከመከሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡ ዲፕሎማቶቹ ግብጽ ከመሄዳቸው በፊት ባለፈው አርብ በአዲስ አበባ የነበሩ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ከውጭ ጉዳይና ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ነበር ወደ ግብጽ ያቀኑት፡፡ ለቱርክ የዜና አገልግሎት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ‹‹ ዲፕሎማቶቹ አዲስ አበባ ደርሰዋል ከካይሮ ይዘውት የመጡትን ሪፖርት እንጠብቃለን ፤ ግብጽ የሶስትዮሹን ውይይት መቀጠል ፍላጎት ካላት እጃችንን ዘርግተን እንቀበላታለን ፤ ሌላ ሃሰብ ካቀረበችም የሀገርን ጥቅም የማየጎዳ አስከሆነ ድረስ በቀረበው ሃሳብ ይ ጥናት አድርገን ውሳኔያችንን ማሰወቅ እንችላለን ›› ብለዋል፡፡ See More Here...diretu.be/462277
Posted on: Tue, 20 May 2014 21:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015