Unity for Democracy and Justice Held a Demonstration in Addis ... - TopicsExpress



          

Unity for Democracy and Justice Held a Demonstration in Addis ... See at ... diretu.be/226572 | አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ‹‹ የእሪታ ቀን ›› በሚል በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መነሻቸውን ቀበና ከሚገኘው የፓርቲው ፅህፈት ቤት አድርገው እስከ አቧሬ መስመር የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞቹ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን ፣ የታሰሩ የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች ይፈቱ ፣ የውሃ ፣ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ይስተካከል ፣ በትራንስፖርት ችግር ዜጎች ሊጎሳቆሉ አይገባም የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል። የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በሰልፉ ማጠናቀቂያ ላይ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር እንዲወያይም እንፈልጋለን ፤ መንግስት በሰልፈኞቹ የቀረቡትን መፈክሮች ተቀብሎ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
Posted on: Sun, 04 May 2014 16:05:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015