Unused government properties worth the annual foreign aid and loan - TopicsExpress



          

Unused government properties worth the annual foreign aid and loan the country gets: FEACC study ... See at ... diretu.be/284846 | ‹‹የውጭ ብድርና ዕርዳታ ያለሥራ ከተከማቹ የመንግሥት ንብረቶች ጋር ተመጣጣኝ ሆኗል›› የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመንግሥት መሥርያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ያለሥራ ተከማችተው የሚገኙ ንብረቶች አገሪቱ በየዓመቱ በዕርዳታና በብድር ከምታገኘው ገንዘብ እንደማይተናነስ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥናት አመለከተ፡፡ ኮሚሽኑ የመንግሥት መሥርያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች የንብረት አስተዳደር ለሙስናና ለብልሹ አሠራር ያለው ተጋላጭነት ላይ ያዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ድርሻ ውስጥ እስከ 14 በመቶ የሚደርሱት የተለያዩ አገራዊ ተግባራትን ለማከናወን በግብዓትነት የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ ንብረቶች ናቸው፡፡ የመንግሥት ተቋማት ከሚመደብላቸው በጀት ውስጥ ከ60 አስከ 70 በመቶ የሚሆነው ለዕቃና ለአገልግሎት ግዥ ተግባር የሚውል ቢሆንም፣ ከፍተኛ በጀት የፈሰሰበት የመንግሥት ንብረት ከብክነት፣ ከብልሽትና ከስርቆት ለመከላከል የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ በየተቋማቱ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ግዥ በከፍተኛ ወጪ እንደሚፈጸም፣ የተገዙ ንብረቶች ከአያያዝ ጉድለት ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ለብክነትና ለግለሰቦች የግል ጥቅም ማግኛ መዋላቸውንም አቶ ወዶ አስረድተዋል፡፡ በመንግሥት ተቋማት በሚታየው የንብረት አስተዳደር ለሙስና ተጋላጭነትና ብልሹ አሠራር ላይ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተወያዩት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ፣ ‹‹ከምንም በላይ የራሳችሁን ጓዳ መፈተሽ አለባችሁ፡፡ ችግሩ የጋራና አሳሳቢ ነው፡፡ ሆኖም መቅረፍ ይቻላል፤›› ብለዋል ሶል የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ ለዝርዝሩ .... diretu.be/284846
Posted on: Sun, 18 May 2014 09:00:00 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015