Woman found dead, wrapped in blanket, lost friend to stabbing six - TopicsExpress



          

Woman found dead, wrapped in blanket, lost friend to stabbing six weeks earlier ራሄል ንጉሴ የተባለች በአሜሪካ የምትኖር ወጣት ተገድላ በብርድ ልብስ ተጠቅልላ ተገኘች፡፡ ራሄል ንጉሴ የተባለችው የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከተገደለች በኋላ አስከሬኗ በብርድ ልብስ ተጠቅልሎ ነው ጫካ አካባቢ የተገኘው፡፡ ራሄል ከመገደሏ ስድስት ሳምንት አስቀድሞ የ46 አመት የሆነችው ቶዋነዳ ሃሪስ በጩቤ ተወግታ ተገድላ የነበረ ሲሆን ይህችው ግለሰብ በምትገደልበት ወቅት ራሄል በአካባቢው እንደነበረች እና ስለ ገዳዩም ለፖሊስ መረጃ መስጠቷ ተገልጿል፡፡ በራሄል ሞት የተነሳ በጩቤ የተገደለችው የቶዋነዳ ሃሪስ ባለቤት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልገው በመሆኑ ከእስር ተለቋል፡፡ ራሄል ንጉሴ በስኳር ህመም ትሰቃይ እንደነበረ ወንድሟ የገለጸ ሲሆን ቀስ በቀስ የአልኮል ሱሰኛ መሆኗን እና የ10 ዓመት ሴት ልጅ እንዳላትም ተናግሯል፡፡
Posted on: Thu, 26 Jun 2014 08:39:50 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015