መንግስት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ዝምታ - TopicsExpress



          

መንግስት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ዝምታ እንዳስደነገጠው ለካድሬዎቹ ገለፀ ፡፡ መንግስታዊ ሽብሩም በወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል ፡፡ #Ethiopia #EthioMuslims ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ደረጃ በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይየመንግስት ሃላፊዎች የክፍለ ከተማአመራሮችንና የየወረዳ ካቢኔዎችን በመሰብሰብ ስለፀጥታ ባወያዩበት ወቅት መንግስት ከኢድ አልፈጥር ጀምሮ በወሰደው የሀይል እርምጃ የሙስሊሙ ተቃውሞ ጋብ ማለቱ ጥሩ ቢሆንም ዝምታቸውም ቢሆን ሊያዘናጋን አይገባም ብለዋል ፡፡ የወረዳ ካቢኔ አባላትንና የክፍ ከተሞች አመራሮችን የሰበሰቡት የመንግስት ሃላፊዎቹ እንደገለፁት “ አሁን ያለው አንፃራዊ ሰላም ተጠብቆ እንዲቆይ ሙስሊሙን የማሸበር ስራ በየክፈለከተማችሁና ወረዳችሁ ተጨባጭ ሁኔታ ስሩ ፡፡ የማሸማቀቅ ፣ የማሳደድ ስራ ስትሰሩ ሙስሊሙ ለተቃውሞ ጊዜ አይኖረውም ፡፡ ሰላም እንዳይሰማቸው ማድረግ አለባችሁ ፡፡ አሁን የተያዘው አቅጣጫ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ” ብለዋል ፡፡ ሌላኛው የመንግስት ሃላፊ በበኩላቸው “ መንግስት በወሰደው እርምጃ ሙስሊሙ ለጊዜውም ቢሆን ዝምታን መምረጡ የሚፈለግ ጉዳይ ቢሆንም ዝምታቸውን ግን በቸልታ የምናየው ከሆነ በጣም አደጋ ነው ፡፡ ድምፃችን ይሰማ ተቃውሞው ለጊዜው ቆሟል ማለቱ ምንም ማለቱ እንደሆነ ግልፅ ባለመሆኑ ስራችንን እንዳጠናቀ ሰው መተኛት የለብንም ፡፡ የድምፃችን ይሰማ አባላትም ውስጥ ለውስጥ ምን እየሰሩ እንደሆነ እንኳ አናውቅም ፡፡ ዝምታቸውን መጠርጠር በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡እንደውም ለኛ ቢጮሁ ነው የሚሻለን ፡፡ ሲጮሁ ግልፅ አጀንዳቸውን እናውቃለን ፡፡ ዝምታቸው ግን ምንም የሚገልፅ ነገር ስለሌለው በአሁን ሰዐት ምን እያደረጉ እንደሆነ እንኳ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር የለም ፡፡ ስለዚህ በየአካባቢያችሁ የሙስሊሞቹን አዋዋል የመከታተል ሃላፊነት አለባችሁ ፡፡ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለባችሁ ” የሚል በፍራቻ የተሸበበ ገለፃ ማድረጋቸውታውቋል ፡፡ ከላይ ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች ታች ሉ የመንግስት አመራሮችን በማደናበር የስራ ጫና ከመፍጠራቸውም በላይ ሌሎች የልማት ስራዎችን ሁሉ እርግፍ አድርገው ትተው ዜጎችን በማሸማቀቅ ተግባር ውስጥ እንዲሳተፉ ግፊት ማድረጋቸው ሀገሪቱ ከደርግ ስርዐት በባሰ ችግር ውስጥ እየገባች እንደሆነ አመላካ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ለፍትህ ሬዲዮ ገልፀዋል ፡፡
Posted on: Sun, 22 Sep 2013 10:01:22 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015