ሙስሊሙ ህብረተሰብም ቢሆን - TopicsExpress



          

ሙስሊሙ ህብረተሰብም ቢሆን ኮሚቴዎቻችንን በሙሉ በነጻ ከማሰናበት ውጭ ያለን ማንኛውም ውሳኔ አይቀበልም፡፡ #Ethiopia #EthioMuslims የእንቅስቃሴውን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስኑ በርካታ ጉዳዮች ሲኖሩ መንግስት በእፎይታው ጊዜ ከተከተለው መንገድ በተጨማሪ በህዳር 23 በመሪዎቻችን ላይ የሚሰጠው ብይንም ትልቅ ግብዓት ይሆናል፡፡ የህዳር 23 ብይን መንግስት የእስከዛሬውን ግትር አቋሙን ገፍቶ እየቀጠለ መሆን አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም ቢሆን ኮሚቴዎቻችንን በሙሉ በነጻ ከማሰናበት ውጭ ያለን ማንኛውም ውሳኔ አይቀበልም፡፡ እንደተለመደው ኮሚቴዎቻችንን በማን አለብኝነት በቀጠሮ ማጉላላት ወይም ጥፋተኛ ብሎ መወሰን መንግስት እየተከተለ ያለውን ፀረ- ኢስላም ፖሊሲ ገፍቶ መቀጠሉን በድጋሚ የሚያረጋግጥ ተግባር ስለሚሆን ይኸው ውሳኔ እንቅስቃሴያችን የወደፊት ጉዞውን አስመልክቶ ካስቀመጣቸው አማራጭ አቅጣጫዎች የመምረጥ ሂደት ላይ ጉልህ ሚና ይኖረዋል! #ድምጻችንይሰማ
Posted on: Sun, 24 Nov 2013 19:01:31 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015