ማሳሰቢያ (ለጎንደር እና ደሴ ከተማ - TopicsExpress



          

ማሳሰቢያ (ለጎንደር እና ደሴ ከተማ ነዋሪዎች) -------------------------------------------------------------------------- “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የሚል መሪ ቃል በማንገብ ዕሁድ በሚካሄደዉ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ ሁሉም ተሳታፊ የሚከተሉትን ተግባራት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ 1. ሰልፉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ፡፡ የተለያዩ ትንኮሳዎች ቢፈታተኑንም እንኳን ሰልፉ ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ እና ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ማካሄድ ይገባል፡፡ አንድ ጠጠር እንኳን ፍፁም መወርወር የለበትም፡፡ 2. የተመረጡ መፈክሮችን ብቻ ማሰማት፡፡ 3. በሰልፉ ወቅት አላስፈላጊ ተግባር የሚፈፅሙ ካሉ ማጋለጥ 4. ስድብን እና አላስፈላጊ ቃላትን ከመጠቀም መቆጠብ 5. የቻልን አበባ (ይህ የበለጠ ይመረጣል) ያልቻልን አረንጓዴ ቅጠል ይዞ ከቤት መዉጣት ፤ በሰልፉ ላይ ከፍ አድርጎ ማዉለብለብ፡፡ ሰልፉ ሲጠናቀቅ የያዝነዉን አበባ ወንድሞቻችን ለሆኑት የፀጥታ አስከባሪዎች/ፖሊሶች የፍቅራችን መግለጫ እንዲሆን በገፀ-በረከትነት ማበርከት፡፡ 6. የሚቻል ከሆነ ነጭ ልብስ መልበስ 7. አንድ እጅን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ሦስት እጣቶችን ማሳየት 8. በማንኛዉም አካል አላስፈላጊ/አፍራሽ ተግባራት ሲፈፀሙ ስናይ ለመረጃ እንዲሆን ፎቶ ማንሳት እንዲሁን በቪዲዮ መልክ መቅረፅ 9. ሰልፉ ሲጠናቀቅ በሰላም ወደ ቤት መመለስ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ Finote nestanet
Posted on: Sat, 13 Jul 2013 07:49:37 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015