ሱረቱ አል-ሐዲድ፤ (የብረት ምዕራፍ) 57:1 - TopicsExpress



          

ሱረቱ አል-ሐዲድ፤ (የብረት ምዕራፍ) 57:1 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው። Whatever is in the heavens and earth exalts Allah , and He is the Exalted in Might, the Wise. 57:2 የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው። His is the dominion of the heavens and earth. He gives life and causes death, and He is over all things competent. 57:3 እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ ነው። He is the First and the Last, the Ascendant and the Intimate, and He is, of all things, Knowing. 57:4 እርሱ ሰማያትንና ምድርን በ6 ቀናት ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ሥልጣኑ) የተደላደለ ነው፤ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን፣ በርሷም ውስጥ የሚያደርገውን፣ ያውቃል፤ እርሱም የትም ብትሆኑ ከናንተ ጋር ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው። It is He who created the heavens and earth in six days and then established Himself above the Throne. He knows what penetrates into the earth and what emerges from it and what descends from the heaven and what ascends therein; and He is with you wherever you are. And Allah , of what you do, is Seeing. 57:5 የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ። His is the dominion of the heavens and earth. And to Allah are returned [all] matters 57:6 ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፤ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነው። He causes the night to enter the day and causes the day to enter the night, and he is Knowing of that within the breasts. 57:7 በአላህና በመልክተኛው እመኑ፤ (አላህ) በርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፤ እነዚያም ከናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው። Believe in Allah and His Messenger and spend out of that in which He has made you successors. For those who have believed among you and spent, there will be a great reward. 57:8 መልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን፣ (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም የያዘባችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑት ለናንተ ምን አላችሁ? የምታምኑ ብትሆኑ፣ (ወደ እምነት ቸኩሉ)። And why do you not believe in Allah while the Messenger invites you to believe in your Lord and He has taken your covenant, if you should [truly] be believers? 57:9 እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የሆኑን አንቀጾች በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው፤ አላህም ለናንተ በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው። It is He who sends down upon His Servant [Muhammad] verses of clear evidence that He may bring you out from darknesses into the light. And indeed, Allah is to you Kind and Merciful. 57:10 የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ መንገድ የምትለግሱትም ለናንተ ምን አልላችሁ? ከናንተ ውስጥ፣ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው፣ (ከተከፈተች በኋላ ከተከፈተች በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይተካከልም፤ ከነዚያ በኋላ ከለገሡትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፤ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው። And why do you not spend in the cause of Allah while to Allah belongs the heritage of the heavens and the earth? Not equal among you are those who spent before the conquest [of Makkah] and fought [and those who did so after it]. Those are greater in degree than they who spent afterwards and fought. But to all Allah has promised the best [reward]. And Allah , with what you do, is Acquainted 57:11 ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው? ለርሱም መልካም ምንዳ አለው። Who is it that would loan Allah a goodly loan so He will multiply it for him and he will have a noble reward? 57:12 ምእምናንና ምእምናትን በስተ ፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)። ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትሆኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)። ይህ ራሱ ታላቅ ዕድል ነው። On the Day you see the believing men and believing women, their light proceeding before them and on their right, [it will be said], "Your good tidings today are [of] gardens beneath which rivers flow, wherein you will abide eternally." That is what is the great attainment 57:13 መናፍቃንና መናፍቃት፣ ለነዚያ ለአመኑት ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና የሚሉበትን ቀን (አስታውስ)፤ ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፤ ብርሀንንም ፈልጉ ይባላሉ፤ በመካከላቸውም ለርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል፤ ግቢው በውስጡ ችሮታ (ገነት) ያለበት፣ ውጭውም ከበኩሉ ስቃይ (እሳት) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር)። On the [same] Day the hypocrite men and hypocrite women will say to those who believed, "Wait for us that we may acquire some of your light." It will be said, "Go back behind you and seek light." And a wall will be placed between them with a door, its interior containing mercy, but on the outside of it is torment 57:14 ከናንተ ጋር አልነበርንምን? በማለት ይጠሩዋቸዋል፣ እውነት ነው፤ ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ፤ (በነቢዩ አደጋዎችን) ተጠባበቃችሁም፤ ተጠራጠራችሁም፤ የአላህም ት እዛዝ እስከመጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ፤ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገሥ) ሸነገላችሁ ይሏቸዋል። The hypocrites will call to the believers, "Were we not with you?" They will say, "Yes, but you afflicted yourselves and awaited [misfortune for us] and doubted, and wishful thinking deluded you until there came the command of Allah . And the Deceiver deceived you concerning Allah. 57:15 ዛሬም ከናንተ ቤዛ አይወሰድም፤ ከነዚያ ከካዱትም መኖሪያችሁ እሳት ናት፤ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (ይሏቸዋል)። So today no ransom will be taken from you or from those who disbelieved. Your refuge is the Fire. It is most worthy of you, and wretched is the destination. 57:16 ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሣጽና ከቁርአንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደተሰጡትና በነርሱ ላይ ጊዜ እንደ ረዘመባቸው፣ ልቦቻቸውም እንደደረቁት ላይሆኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከነርሱም ብዙዎቹ አመጠኞች ናቸው። Has the time not come for those who have believed that their hearts should become humbly submissive at the remembrance of Allah and what has come down of the truth? And let them not be like those who were given the Scripture before, and a long period passed over them, so their hearts hardened; and many of them are defiantly disobedient. 57:17 አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው የሚያደርጋት መኾኑን ዕወቁ፤ ታውቁ ዘንድ አንቀጾችን ለናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ። Know that Allah gives life to the earth after its lifelessness. We have made clear to you the signs; perhaps you will understand. 57:18 የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤በደሩ ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤ ለነርሱም መልካም ምንዳ አላቸው። Indeed, the men who practice charity and the women who practice charity and [they who] have loaned Allah a goodly loan - it will be multiplied for them, and they will have a noble reward. 57:19 እነዚያም በአላህና በመልክተኞቹ ያመኑት፣ እነዚያ እነሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው፤ ለነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፤ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት፣ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። And those who have believed in Allah and His messengers - those are [in the ranks of] the supporters of truth and the martyrs, with their Lord. For them is their reward and their light. But those who have disbelieved and denied Our verses - those are the companions of Hellfire. 57:20 ቅርቢቱ የሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ በገንዘቦችና በልጆችም መፎካከሪያ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆንዋን ዕወቁ፤ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅናም ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ናት፤ በመጨረሻዪቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፤ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም። Know that the life of this world is but amusement and diversion and adornment and boasting to one another and competition in increase of wealth and children - like the example of a rain whose [resulting] plant growth pleases the tillers; then it dries and you see it turned yellow; then it becomes [scattered] debris. And in the Hereafter is severe punishment and forgiveness from Allah and approval. And what is the worldly life except the enjoyment of delusion 57:21 ከጌታችሁ ወደ ሆነች ምሕረት ወርዷ እንደሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፤ ለነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች። ይህ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው። Race toward forgiveness from your Lord and a Garden whose width is like the width of the heavens and earth, prepared for those who believed in Allah and His messengers. That is the bounty of Allah which He gives to whom He wills, and Allah is the possessor of great bounty. 57:22 በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው። No disaster strikes upon the earth or among yourselves except that it is in a register before We bring it into being - indeed that, for Allah , is easy - 57:23 (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በት ዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፤ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሰው አይወድም። In order that you not despair over what has eluded you and not exult [in pride] over what He has given you. And Allah does not like everyone self-deluded and boastful - 57:24 (እነርሱም) እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በሥት የሚያዙ ናቸው፤ (ከውነት) የሚሸሽም ሰው (ጥፋቱ በራሱ ላይ ነው)፤ አላህም እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው። [Those] who are stingy and enjoin upon people stinginess. And whoever turns away - then indeed, Allah is the Free of need, the Praiseworthy. 57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደነርሱ አወረድን፤ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን፤ (እንዲጠቀሙበት) አላህም ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን ሰው ሊያውቅ (ሊገልጽ አወረደው)፤ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና። We have already sent Our messengers with clear evidences and sent down with them the Scripture and the balance that the people may maintain [their affairs] in justice. And We sent down iron, wherein is great military might and benefits for the people, and so that Allah may make evident those who support Him and His messengers unseen. Indeed, Allah is Powerful and Exalted in Might. 57:26 ኑሕን፣ ኢብራሒምንም በእርግጥ ላክን፤ በዘሮቻቸውም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፎችን አደረግን፤ ከነሱም ቅን አለ፤ ከነሱም ብዙዎች አመጠኞች ናቸው። And We have already sent Noah and Abraham and placed in their descendants prophethood and scripture; and among them is he who is guided, but many of them are defiantly disobedient. 57:27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን የመርየምን ልጅ ኢሳንም አስከተልን፤ ኢንጅልንም ሰጠነው፤ በነዚያም በተከተሉት (ሰዎች) ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፤ በነርሱ ላይ (ምንኩስናን) አልጻፍናትም፤ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ (ፈጠሩዋት)፤ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም፤ ከነሱም ለነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፤ ከነሱም ብዙዎቹ አመጠኞች ናቸው። Then We sent following their footsteps Our messengers and followed [them] with Jesus, the son of Mary, and gave him the Gospel. And We placed in the hearts of those who followed him compassion and mercy and monasticism, which they innovated; We did not prescribe it for them except [that they did so] seeking the approval of Allah . But they did not observe it with due observance. So We gave the ones who believed among them their reward, but many of them are defiantly disobedient. 57:28 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ በመልክተኛውም እመኑ፤ ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና፤ ለናንተም በርሱ የምትኼዱበት የሆነ ብርሃንን ያደርግላችኋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነው። O you who have believed, fear Allah and believe in His Messenger; He will [then] give you a double portion of His mercy and make for you a light by which you will walk and forgive you; and Allah is Forgiving and Merciful. 57:29 (ይህም) የመጽሐፉ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውን ችሮታም በአላህ እጅ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል ማለትን፣ እንዲያውቁ ነው፤ አላህም ታላቅ የችሮታ ባለቤት ነው። [This is] so that the People of the Scripture may know that they are not able [to obtain] anything from the bounty of Allah and that [all] bounty is in the hand of Allah ; He gives it to whom He wills. And Allah is the possessor of great bounty. Copyright 2013, AmharicQuran
Posted on: Tue, 27 Aug 2013 10:54:22 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015