*^* ‹‹ ሴት ልጅ ነፍስ አላትን?!›› *^* - TopicsExpress



          

*^* ‹‹ ሴት ልጅ ነፍስ አላትን?!›› *^* ‹‹ ሴት ልጅ ነፍስ አላትን?!›› ብለው በ13 ክፍለ ዘመን የነበሩት የክርስቲያን ቀሳውስት ጳጳሳት ወ.ዘተ››ተጨቃጭቀው እንደነበር የታሪክ ምሁራን ጽፈዋል፡፡ ለዛሬ ትንሽ ካነበብኩት ላካፍላችሁ ……….*^* *^* ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እውነተኛ የሴቶች ነፃ አውጪ!!*^* ** ስለ ሴቶች ብዙ ተብሏል ፡፡ ዛሬም እየተባለ ይገኛል፡፡ የኢስላም ጠላቶች ኢስላምን የሴቶች በዳይ እያስመሰሉ ማቅረቡን ገፍተውበታል ነብዩ ሙሐመድ የአላህ ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና የሴቶች ጠበቃ እንዳልነበሩ ሁሉ ፀረ-እንስት አድርገው ለማቅረብ ሌት ተቀን ለፍተዋል፡፡ እየተለፋም ይገኛል፡፡ ይቀጥሉበትም ይሆናል፡፡ ለነገሩማ እኛ ሙስሊሞችስ ብንሆን የኢስላምን ትክክለኛ ገጽታ ለሌላው ለማስተዋወቅ መቼ ሞከርንና? በራሳችንስ ቢሆን ኢስላምን መች ተላበስንና ? ስለ እምነቱ ለማወቅስ መች ተጋንና? ኢስላምና ሙስሊሞች አራምባና ቆባ ሆንና ለፀረ-ኢስላም ሃይላት በእሳት ላይ ጭድ ጨመርንና አረፈው እንጂ፡፡ ሌላው ቀርቶ በአንዳንድ ፔጆች ላይ እና ግሩፖች ላይ አንዳንድ እህቶችና ወንድሞች አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸውና ይህን አስተሳሰብ ለማስቀራት ኢስላም ላይ ለሚነሱ ትችቶች አቅማቸው የቻለውን ጽፈው ፖስት ሲያደርጉ እኛ እንኳን ጽፈን እንደነሱ መስራት ባንችልም እነሱ የጻፉትን አንብቦ ሌሎች እንዲያነቡት ሼር በማድረግ ለሌሎች አስተላልፎ የተዛቡ አመለካከቶችን ለማስወገድ መሞከር እንኳ ‹‹ዳገት›› ሆኖብናል፡፡ ምክኒያቱ ግን አይገባኝም፡፡ አላህ ይዘንልን!! እ.ኤ.አ በ 1979 ሚያዘዝያ 16 በወጣው ታይም መጽሔት ዘገባ መሰረት የኢስላምን ስም ለማጉደፍ በአንድ መቶ ሀምሳ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማለትም ከ1800-1950 በምዕራባዊያን ክርስቲያኖች ከ60,000 (ስልሳ ሺህ) በላይ መጽሐፍት ተጽፏል፡፡ በቀን ስናሰላው በየቀኑ ከአንድ መጽሐፍት በላይ ተፅፏል ማለት ነው፡፡ ስለ ኢስላም የተሳሳተ ግንዛቤን ለመፍጠር ከኦሬንታሊስቶች ባሻገር አማኝ መሆናቸውን የሚናገሩት ክርስቲያኖችም እምነታቸውን ይበልጥ ጥሩ አስመስሎ ለማቅረብ በመጽሐፍ መልኩ ሆነ በተለያዩ ኢንተርኔት ድህረ ገጾች በመልቀቅ በፈጠራ የተሞላ ፕሮፖጋንዳ በኢስላም ላይ መንዛት እንደ እስትራቴጂ ተያይዘውታል :: ለነገሩማ የክርስትና መስራቹ ጳውሎስ፡- ‹‹በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈረድብኛል?›› (ወደ ሮሜ ሰዎች 3፡7-8) ብሎ የለ? አንፈርድባቸውም፡፡ እኛ ሙስሊሞች ግን እነሱ በኢስላም ላይ የሚያነሱትን ቅጥፈቶች አቅማችን በፈቀደው ሁኔታ እውነታውን ለእውነታ ፈላጊ ማህበረሰብ ማድረስ አለብን ሌላው ቢቀር ሌሎች የሚጽፉትን ሼር በማድረግ የአቅማችንን እናድርግ እላለሁ፡፡{አላህ የበለጠ ያውቃል!! } ነገርን ነገር ያነሳዋል አይደል የሚባለው እግረ መንገዴን አነሳሁነት እንጂየጹሁፌ ርዕስ ይህ አይደለም ወደ ጽሁፌ ልግባ፡- *^* ‹‹እውን ሴት ልጅ ነፍስ አላትን?!›› ብለው ይጨቃጨቁልናል በ13 ክፍለ ዘመን የነበሩት የክርስቲያን ቀሳውስት ጳጳሳት ወ.ዘተ. ትንሽ ካነበብኩት ላካፍላችሁ ……….*^* ** ከክርስቲያኑ ዓለም “ሴቶች ነፋስ አላቸዉ ወይስ የላቸውም? ሰውስ ናቸዉ አይደሉም” በማለት ይጨቃጨቁ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስነብቡናል የ13ኛ ክፍለ ዘመን የክርስትና ምሁር ቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ ፈጣሪ ሴትን በመፍጠሩ ተሳስተ ሲል እንዲህ በማለት ይገልጻል፡– ‹‹በመጀመሪያ በነገሮች አፈጣጠር ላይ ሴትን እንደመፍጠር የተፈጠረ ስህተት የለም፡፡ ሴት ባልተፈጠረች(ይሻል) ነበር፡፡(Saint Thomas Aquinas, Summa Theological, MCG raw Hill, Eyre & spottis woode, p.35) ** በቀደምት ክርስቲያናት ምሁራን ዘንድ የሴቶች ተፈጥሮ ብዙ ያጨቃጨቀ፤ የተጻፈበትና አያሌ ውይይቶች ያስተናገደ አብይ ጉዳይ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ነፍስና የማሰብ ችሎት የላቸውም በማለት ከእንስሳ መድበዋቸዋል፡፡ ይህም በዚህ መልኩ ተዘግቧል፡- ‹‹In the year 584 CE, in Lyons, France, forty-three Catholic bishops and twenty men representing other bishops held a most peculiar debate; ‹‹Are women Human?›› After many lengthy arguments a vote was taken. The result was thirty- two, yes; thirty-one, no. women were declare human by one vote!›› (Thorpe, p.542; Dalton, 2,p.345; Latouche, 2p,151 and Thirty-seven religious reasons to hate women) ‹‹ሴቶች ሰው ናቸውን?›› ለሚለው ክርክር መፍትሄ ለማበጀት አርባ ሦስት ከካቶሊክ እና ሃያ ከሌሎች አብያተክርስትያናት የተወከሉ በአጠቃላይ ስልሳ ሁለት ጳጳሳት የተሳተፉበት ጉባኤ እ.ኤ.አ በ584 በሊዮን-ፈረንሳይ ተካሄደ፡፡ ከብዙ እልህ አስጨራሽ ክርክር በኋላ ሰላሳ ሁለት ጳጳሳት ‹‹አዎ›› ሲሉ ሰላሳ አንዱ ደግሞ ‹ ነፍስ የላትም›› ሲሉ ድምጽ ሰጡ፡፡ በጠባብ ልዩነት በአንድ ድምጽ ሴቶች ‹‹ሰው›› ናቸው ተብሎ ሊወሰን በቅቷል፡፡ ሴቶች ‹‹ሰው›› ናቸው በማለት በአንድ ድምጽ ልዩነት የተወሰነበት ጉባኤ ካበቃ በኋላ ‹‹እሺ ሴቶች እንደ ወንዶች ነፍስ(ሶውል) አላቸውን?›› የሚለው ክርክር በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እጅጉን ተስፋፋ ፡፡ ይህንንም በጉባኤ ለመወሰን እና በጉዳዩ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ እ.ኤ.አ በ585 ሀምሳ ዘጠኝ ጳጳሳትን ያሳተፈ ጉባኤ በፈረንሳይ- በማኮን ተደረገ ፡፡ ሴቶች ነፍስም ሆነ የማሰብ ችሎታ የላቸውምና ሰው ሊባሉ አይገባም በሚሉትና በሌላኛው ወገን መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሰው›› ብሎ ጠርጧቸዋልና ነፍስ አላቸው ሰውም ናቸው በሚሉት መካከል ጉባኤው ለሁለት ተከፈለ፡፡ የጋራ አቋምም ሳይዙ ተበተነ፡፡››(Joslyn Gage (1826-1998), Women, church and state, p.56-57) ** ይህ ጉባኤ ከተደረገ ከአንድ ሺህ ዓመት በኋላም እንኳ የነበሩት አንዳንድ ክርስትያን ምሁራን ሴቶች ከወንዶች እኩል የሆነ ነፍስ አላቸው ብለው አያምኑም ነበር፡፡ ለአብነትም ታዋቂው ሳሙኤል በትለር (እ.ኤ.አ 1612-1680) እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹የሴት ነፍስ ትንሽ ናት፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች ከናካቴው የላትም ብለው ያምናሉ፡፡›› (James McDonald, Universal Declaration of Human Right, Christianity and Women’s Right, 2006) ** ቄስ ጀምስ ፓይክ እንዲህ ብለው ነበር፡- ‹‹ሴቶች ትንሽ ነፍስ/ሶውል/ ነው ያላቸው፡፡ ትንሽ ነገር የሚወድ …. በከተማ ፤ በቤት፤ በጓዳ እና በአስተሳሰብህ ሁሉ ላይ ፍቅሯን ልትለግስህ ግዴታዋ ነው፡፡ አንተ ደግሞ ……‹‹ከፈለክ›› ……ፍቅርህን ትሰጣታለህ፡፡›› (Episcopal Bishop James pike, A letter to his son, 1968) ** የአሜሪካ የሴቶች ፀረ-ሰቆቃ ማህበር መሪ የነበረችው ማቲልዳ(እ.ኤ.አ 1826-1898) እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- ‹‹የዚህ የቀድሞው እምነት ቅሪት በኛው ሀገር (አሜሪካ) እ.ኤ.አ በ1854 በፊላዴልፊያ በተደረገው የሴቶች መብት ኮንቪንሽን ላይ ተንጸባርቋል፡፡ አንድ ተቃዋሚ ከታዳሚው መሀል በጩኸት መጀመሪያ ሴቶች ነፍስ እንዳላቸውና እንደሌላቸው እናረጋግጥ! ሲል ተናግሯል፡፡›› (Ibid, p.57) ** ሮዝመር ራድፎርድ ቅዱስ አውጉስቲን እንዲህ ማለቱን ዘግበዋል፡- ‹‹ሴት ከበሏ ጋር የእግዚአብሐር አምሳል ናት፡፡ ያኔ (ከባሏ ጋር) ሁለመናቸው የእግዚአብሔር አንድ አምሳል ናቸው፡፡ ነገር ግን በወንድ አጋርነቷ ማለትም ሴት ብቻዋን የእግዚአብሔር አምሳል አይደለችም ፡፡ ነግር ግን ወንድ ብቻውን ከሴት ጋር ሆነው እግዚአብሔር አምሳል እንደሚሆኑት ብቻውን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር አምሳል ነው፡፡›› (Shelly Schoepfiln, Women and Christianity: Can Two Walk Together, Except They be Agreed? August, 1997, p.2) ** ጆን እስቱዋርት ሚል ‹‹ዘ ሰብጁኬሽን ኦፍ ውሜን›› በተሰየው ድርሳናቸው ውስጥ የሚከተለውን ጽፈዋለ፡- ‹‹ስልጣኔን ክርስትና ለሴት ልጅ ፍትሐዊ መብቶቿን እንዳስከበሩላት ሁሌም ሳያቋረጥ ይነገረናል፡፡ ይሁን እንጂ ሚስት በተጨባጭ የባሏ ገባር አገልጋይ ናት፡፡ ሕጋዊ ግዴታው እስከ ሚያስኬደው ድረስ ባሮች ተብለው በተለምዶ ከሚጠሩት የተለየች አይደለችም፡፡›› (The Encyclopedia Briticanica, 1902, vol. 3, p.2942) ይህም አልፏል ይገርማል!! አላህ ሱ.ወ እድሜ ከኢማን ጋር ይስጠን እንጂ ገና ብዙ እናነባለን. ** በኢስላም ታሪክ ውስጥ ማንም ሙስሊም የሴትን ስብእና ሁኔታ ወይም ነፍስና ሌላ መንፈሳዊ ባህሪያት ያላት መሆኑን በፍጹም አልተጠራጠረም፡፡** *^* ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ተልከው መጥተው ስለሴቶች መብት አስተምረዋል፡፡ ቀደምት የነበሩት የክርስቲያን ምሁራን ኢስላም ‹‹ለሴቶች ከሚገባቸዉ በላይ መብት ሰጠ›› ነበር ትችታቸዉ፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይና መነኩሲት የነበረችው እና በሃይማኖቶች ታሪክ ላይ በለንደን ዩኒቨርሲቲ መምህርት የሆነችው ከረን አርም እስትሮንግ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- “በምእራባውያን መስቀለኞች ይዞታ የነበሩት ክርስቲያኖች እንዴት ሴቶቻቸውን እንደሚያስዳድራቸው ሙስሊሞች ሲመለከቱ ተሸበሩ፣ የክርስቲያን ምሁራንም እንደ ባሪያና ሴቶች ላሉት ዝቅተኛ ክፍሎች ኢስላም ከሚገባቸው በላይ መብት ሰጠ በማለት ኢስላምን አወገዙ፡፡”( (Karan Armstrong Muhammed, a biography of the prophet, p. 199) ** ‹‹በአጠቃላይ የነቢዩ ሙሐመድ መምጣት በሴቶች በህይወት ላይ እጅግ ከፍተኛ ለውጥን አጐናጽፏል፡፡ ይህንንም ከመሰከሩት ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑት ኘሮፌሰር በርናርድ ሊዊስ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- “በአጠቃላይ የኢስላም መምጣት ለቀድሞዋ አረቢያ ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ በነበራቸው ስፍራ ላይ እጅግ ብዙ መሻሻልን አስከትሏል፡፡ ንብረት የመውረስና ለሎች በርካታ መበቶችንም አጐናፅፏቸዋል፡፡”›› (293 Bernard Lewis, The Middle East, p.210) **‹‹ነቢዩ መሐመድ ጠፍቶና ተረስቶ የነበረው የፈጣሪ ሃይማኖትን ኢስላምን ለማዳረስ ከመላካቸዉ በፊት በቀድሞው አረቢያ ምድር ኑሮ ለሴቶች ምን እንደሚመስል በለንደኑ የቤክ ኮሌጅ መምህርት የሆነችው ኘሮፌሰር ከረን አርምስትሮንግ እንዲህ ትገልፃለች፡- “የግድ ልናስታውስ የሚገባነ ሴት ልጅን ከነህይወት መቅበር ልማድ በነበረበት በምንም መልኩ መብት ባልነበራቸውና የበታች ፍጥረት እንደባሪያ ተደርገው በቀድሞሞ አረቢያ ሴቶች በሚታዩበት ጊዜ ሙሐመድ ለሴቶች የዋለው ውለታ ልዩ ነበር፡፡ በተለይ ህዝቡን ያስገረመው የድርሻቸውን መውረስና ምስክር መሆን ይችላሉ ማለቱ ነበር፡፡››” (Karan Armstrong Mohammed, a biography of the prophet, p. 191) ** ዶ/ር ቢሳንት እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- “ኢስላም መጥፎ ሃይማኖት ነው፡፡ ምክንያቱም እሰከ አራት ሚስት ማግባት ፈቅዶአልና” ሲባል ትሰሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በአንድ ወቅት በእንግሊዝ ፖርላማ ያደረግኩትን ንግግር አልሰማችሁ ይሆናል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነበር፡- አንድ- ለአንድ በሚል መመሪያ ስር የሚፈጸሙት አያሌ ዝሙቶች ውሰን ሚስቶች ከማግባት የበለጠ መናፍቃንነትና ብኩንነት ነው በማለት ተናገርኩ፡፡ እንደተለመደው ይህ አይነቱ ንግግር ምን ያህል ምዕራባውያን አድማጮችን እንደሚያስቆጣ አውቅ ነበር፡፡ ቢሆንም ሃቁን መናገር ነበረብኝ፡፡ ምክንያቱም ኢስላም ሴቶችን በሚመለከት የደነገገው ህግ ሌሎች ካረቀቋቸዉ ደንቦች የተሻለና መጣም ፍትሃዊ የሆነ መሆኑ መታወስ ስለሚገባው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢስላም የሴቶች ህግ በጥቂቱ ከእንግሊዝ አገር የሴቶች ህግ ጋር እየተዛመደ ነው፡፡ ስለንብረት ባለቤትነት፣ የውርስ መብት፣ የፍች ህግነት፣ ወ.ዘ.ተ በተመለከተ የኢስላም ህግ ከምዕራቡ ህግ በጣም የላቀ ነው፡፡ ሰዎች ከአንድ በላይ ማግባትና አንድ ለአንድ በሚሉት ቃላት የታወሩ ይመስላሉ፡፡ አንድ -ለአንድ ከማለው የጋብቻ ደንብ በስተጀርባ ያሉትን ማህበራዊ እንቅፋቶች መመልከት አልቻሉም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ከአንድ በላይ በማግባቱ ሊፈቱ የሚችሉተን ማህበራዊ ችግሮች እንደዚሁ መገንዘብ አልተቻላቸውም፡፡ በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለም የተከሰተውነ የሴት ልጅን ፋይዳ ማጣት ይኸውም በመጀመሪያ ፍቅረኛዎቻቸው እንደሸንካራ ተመጠው የተተፉት ሴቶች እንዲሁም በየጐዳናው ያለምንም ጥበቃና እንክብካቤ መንከራተት እጣቸዉ የሆኑትን ሴቶች ማስታወስ አልቻልንም፡፡ “ (Annie Besant, the life & Teachings of Muhammed Madrase, p 3)
Posted on: Thu, 18 Sep 2014 06:18:06 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015