በሂጅራ ግቢ ታስረው የሚገኙት - TopicsExpress



          

በሂጅራ ግቢ ታስረው የሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ድንቅ የኢስላም ልጆች የታላቁን ረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ሙስሊሞች በተወካዬቻቸው በኩል የእርዳታ ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ በሂጅራ ግቢ በእስር ላይ የሚገኙት ኮሚቴዎቻችን፣ ዳዒዎቻችን፣ ኡስታዞቻችን አርቲስቶችና ሌሎች ወንድሞቻችን በአንድነት በመሆን ለተቸገሩ ወገኖች ጧሪ ለሌላቸው ሽማግሌዎች፣ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች፣ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩና ለየቲሞች የእርዳት እጃቸውን በተወካዮቻቸው በኩል መስጠታቸውን ምንጮቻችን አስታውቀዋ፡: እነዚህ ውድ የኢስላም ልጆች ይህንን ድጋፍ በተከበረው ወር መግቢያ ላይ ያደረጉት በርካታ ሙስሊም ችግረኞች ፆማቸውን በአግባቡ እንዲፆሙና ሃይማኖታዊ ግዴታዎቻቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ በማሰብ ጭምር ነው :: በመጨረሻም እያንዳንዱ ሙስሊም ህብረተሰብ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ለአኼራው መሰነቀ እንደሚገባውና እነዚህን ችግረኞች በየአካባቢያችን በመርዳትና ችግራቸውን በመቅረፍ ላይ መተባበር እንደሚገባን አበክረው ገልፀዋል :: ሀገራችን ላይ እየደረሰብን ያለውን የህግ ጥሰትና የመብት ረገጣ አላህ እንዲያነሳልን በዱዓ መበርታት እንደሚያስፈልግ አደራ ማለታቸውን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። አላሁ አክበር!!!!! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ for more information visit this page https://facebook/abudawdosman https://facebook/abudawdosman
Posted on: Tue, 09 Jul 2013 20:18:23 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015