በሞቅታ መንፈስ የተፃፈ!!!! ለማስታወቂያ - TopicsExpress



          

በሞቅታ መንፈስ የተፃፈ!!!! ለማስታወቂያ የተመረቱ ልብሶችን ፣ ለፍተን ፣ ጥረን የምንገዛ ሕዝቦች ነን!!! (አራት ነጥብ!!!) በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጁ የምንባል ወይም የተጀራን ሰዎች ነን!!! አማራጭ መንገድ ተሰርቶላችኋል ….. እንደፈለጋችሁ መሄድትችላላችሁ !! የተባልን ሰዎች ነን!!!! ሲም ካርድ በ30 ብር ማግኘት የምንችል ሕዝቦች ነን!!!! (ኔት ወርክ ግን በሶስት ሺህ ብር የማናገኝ) ለሶስት ቀናት ውሃ ይጠፋል ብንባል ዝም ብለን ውሃ እስኪመጣ የምንጠብቅ “ታጋሽ” ሕዝቦች ነን!!! (ባይመጣም ምንአባቱ!!!!) ቅንጅት ባስደነበረው መንግስት የምንመራ ሕዝቦች ነን!!! (መደንበሩ በፈጠረው ድንጋጤ ያገኘውን መንገድ በመቆፈር ይኸው ማለፊያ ማግደሚያ እስክናጣ ድረስ መፈናፈኛ አሳጥቶናል¡¡¡) ይኛንም እንዲህ ለመዘመር ያብቃን!!!! “የማያልፉት የለም ያ ሁሉ አለፉ ታማኝ የሕዝብ ልጅ ፣ በደሙ በላቡ ደማቅ ታሪክ ጻፈ!!!!”
Posted on: Tue, 17 Sep 2013 19:09:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015