በሴቶች አእምሮ ውስጥ ምን እየተካሄደ - TopicsExpress



          

በሴቶች አእምሮ ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው? “የሰው ልጅ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መጥቆ፡ በጥናትና ምርምር ረቅቆ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲደርስ(የመጨረሻ ደረጃ የሚባል ካለ) የጥናት መስኩ የሚያተኩርበት ርዕስ rocket science፡ quantum physics ወይንም ደግሞ artificial intelligence አይሆንም” ይላሉ ምሁራን። “ሳይንቲስቶችን ቀን ከሌት የሚያሳስባቸው nanotechnology እና genetic engineering ይሆናሉ ተብሎም አይጠበቅም” ብለው ያስረዳሉ። “ተመራማሪዎችን እንቅልፍ የሚነሳቸውና የሚያወዛግባቸው ከፊዚክስ ህግ ያፈነገጡ፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ተዓምራቶች ይሆናሉ ተብሎም አይገመትም።” ብለውም ይጨምራሉ። “ያኔ አትኩሮቶች ከፍጥረት ሁሉ ተወዳዳሪ ወደሌለው ወደሰው ልጅ ብቻ ያመለክታሉ፤ የሰውን ልጅ ስነ-ልቦናዊ ባህርያት በመተንተን ላይ ያተኩራሉ።” ብለውም ይደመድማሉ። ከአድማሱ ባሻገር፡ ከሰፊው ጠፈር ወዲያ ስላለው አለም፡ መልስ ሊሰጠን የሚችለው አንድና ብቸኛው መፍትሄ ብሩሕ ጭንቅላት ብቻ ነው። በአካል የማንደርስባቸው ሩቅ ቦታዎችን፡ በመንፈስ ብቻ ተጉዘን የምናስሳቸው፤ ቦታ እና ግዜ ተጽእኖ በማያሳርፉበት፡ቁስም ሆነ ሌሎች ሁኔታዎች ከማያግዱት፡ በረቂቁ ምናባችን ብቻ ነው። ፈጣሪም ከሰው ልጅ የሚስተካከል አንዳች እንኳን አልፈጠረም። የፈጣሪ masterpiece እኛው ነን። እዚች ጋ አንድ ጨዋታ ላስገባላችሁ፦ “ፍሩይድ የአእምሮ ልቀት እና ምጥቀት አለም አቀፍ ምልክት ተደርጎ የሚወሰደውን አንስታይንን ይቀድመዋል” አለኝ አንዱ። “እንዴት?” ጠየቅኩ። “አንስታይን ወደ ውጭ ነው የተመለከተው። ፍሩይድ ግን ወደ ውስጥ፡ ወደ ውስጠኛው ውስጥ ነው ያየው” አለኝ። መላሹ እውነት አለው። ለዋና ዋና ችግሮቻችን መፍትሄ የሚመዘዘው ከውስጥ ብቻ ነው። “ምክንያቱስ?” ካላችሁ እነዚሁ ችግሮቻችንም ያሉት ከውስጥ ነውና። ወደ ውጭ መመልከታችንን በቀጠልን ቁጥር፡ ከውስጥ ያለው ችግራችን እየተስፋፋ፡ ስር እየሰደደ ይሄዳል።ከስረ-መሰረቱ መንግሎ ለመጣልም በዚያው መጠን እየከበደ ይመጣል። ከውስጥ ያሉት ጦርነቶች እየከሰሙ፡ ሰላም በውስጣችን እየሰፈነ ሲመጣ በውጨኛው አለምም እንደዚያው እየሆነ ይመጣል። ምክንያቱም አለም ሌላ ምንም ሳትሆን የሁላችንም አስተሳሰብ ድምር ውጤት ነጸብራቅ ናትና። ታዲያ ይኸው ተአምረኛ ፍሩይድ ሌሎች ብዙ ነገሮችንም ጨምሮ ነግሮናል፦ ስለ ህልምና አስፈላጊነቱ፡ ስለ ዋናዋናዎቹ የህይወት ሀይሎች፡ ጾታዊ ዝንባሌዎቻችንና በባህርያችን ላይ ስለሚያሳርፉት ተጽእኖ፡ አስተዳደጋችን በቀረው ህይወታችን ላይ ጥሎት ስለሚያልፈው አሻራ እና ሌላም ብዙ ብዙ። ነገር ግን ፍሩይድን ለአመታት ያለፋው አንድ ጥያቄ ነበር፦ “ሴቶች ከምር የሚፈልጉት ምንድነው?” የሚል። እነሆ ሰላሳ አመታት በሙሉ ከፈጀው የፍሩይድ ያልተቋረጠ ምርምርና ጥናት በኋላም መልስ ያልተገኘለት እንቆቅልሽ፤ ተደጋግሞ ቢጠየቅም አንዴም እንኳን መልስ ያልተሰጠበት ትልቅ ጥያቄ ሆኖ ቀርቷል! የሰው ልጅ የመጨረሻ የምርምር እርከን የዛው የሰው ልጅ ስነ-ልቦና ጥናት ነው የሚል ጽንሰ-ሀሳብ ያቀረቡት አሳቢዎች፡ የዚህ የምርምር መስክ የመጨረሻ ምዕራፍ ደግሞ የሴቶች ስነ-ልቦና እንደሚሆን አበክረው ይናገራሉ። በወንዶች አእምሮ እና ሀሳብ ውስጥ ምን እንዳለ ይታወቃል! ሴቶች ናቸው! :P =D በተወሳሰበው የሴቶች አእምሮ ውስጥ ግን ምን እየተካሄደ ይሆን??? ሴቶች ብቻ ያውቃሉ!!! :)
Posted on: Mon, 21 Jul 2014 12:03:26 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015