** በኤፍ ኤም ምናምን ነጥብ ምናምን - TopicsExpress



          

** በኤፍ ኤም ምናምን ነጥብ ምናምን ተጋብዤ Interview ** ከዚህ በታች የምታነበው ፅሑፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ አንድ ታዋቂ አርቲስት Interview ሲደረግለት ሰምቼ ነው:: የሁላችንም ችግር ሳይሆን አይቀርም ብዬ የእራሴን Interview ሰርቻለው:: ጉዳዩ ደግሞ በአየር ላይ እና ከአየር ዉጪ የምንኖረው ሂይወት ልዩነት ነው:: መልካም ንባብ……… እንዴ……. የረሳሁት………… ፅሁፍን ስታነበው ቫትን አያካትትም………… በአንድ ፌዲዮ ላይ ድምፃዊ ሆኜ…….. ጋዜጠኛው;- እሺ….. አርቲስት ኤፍሬም አማረ አድማጮችን አክብረክ እዚህ ስለተገኘክ አመሰግናለው:: እኔ;- (ጉሮሮዬን አፀዳዳው)………. እሺ እኔም አመሰግናለው:: ኮራ ብዬ…….. ጋዜጠኛው;- ዬት ተወለድክ?....... ዬት አደግ?..... ዬትስ ተማርክ?...... እኔ;- የተወለድኩት እዚው አዲስ አበባ ነው: ያደኩትም:: ትምህርት እንደማንኛውም ኢትዮፒያዊ ቄስ ትምህርት ቤት ነው የጀመርኩት:: ከዛን ከ1- 8 እንትን ት/ቤት; 9-10 እዛው ከተማርኩ በኋላ ጥበብ ጠርታኝ ወደ ሙዚቃው ገባው:: (እውነታው ግን ውጤት ስላልመጣልኝ ነው እንጂ ጥበብ ስራ አጣች እኔን የምትጠራው…………) ጋዜጠኛው;- ሙዚቃን እንዴት ጀመርክ? እኔ;- ቤት ውስጥ እና ትምህርት ቤት አንጎራጉር ነበር በተለይ ትምህርት ቤት ዝግጅት ሲኖር እኔ ነበርኩ የምጠራው………….:: (እውነታው ግን ት ቤት ዝግጅት ሲኖር ግቢ ውስጥ አልገኝም) ጋዜጠኛው;- የመጀመሪያ አልበምክ በጣም ተወዶኋል ተሸጦኋልም የህዝቡ feedback እንዴት ነበር አርቲስት ኤፍሬም:: እኔ;- well…. የመጀመሪያ አልበሜን በጣም ነው የደከምኩበት….:: የልፋቴን ዋጋም አግኝቻለው:: የህዝቡ ፍቅር በጣም በጣም ነው ደስ የሚለው realy ምን እንደምልክ አላውቅም… (እንባ ይተናነቅኛል… ጋዜጠኛው አይዞ ይልና ”አድማጮቻችን ኤፍሬም ትንሽ ስሜቱ እስኪረጋጋ ሙዚቃ አድምጠን እንመለስ‘ ይልና የቴዲ አፍሮን ተናነቀኝ እንባ ይጋብዛል……) . . . . ከሙዚቃ ግብዣ በኋላ . . . ጋዜጠኛው;- እሺ አድማጮቻችን ከሙዚቃ ግብዣ በኋላ ተመልሰናል ከአርቲስት ኤፍሬም አማረ ጋር የምናደርገው ቆይታ ይቀጥላል…………. እኔ;- (ትንሽ አልቅሼ ተመለስኩ)… እሺ አድማጮቻችን የህዝብ ነገር ሲነሳ እንባ ይተናነቀኛል ለዛ ነው ይቅርታ እጠይቃለው… (እውነታው ግን ያለቀስኩት ብዙ ሺ ብር አውጥቼ የሰራሁት የሙዚቃ አልበም ባለመሸጡ ነው ተናነቀኝ እንባ….) ጋዜጠኛው;- እሺ አድማጮቻችን እንቀበል...ሄሎ ማን እንበል… አድማጭ;- ሄለን……… እባላለው ከፒያሳ ነው…………. ሄሎ ኤፍሬም … እኔ;- አቤት ሄሊ…… ሄለን;- በጣም በጣም አድናቂክ ነኝ… የኔ ቆንጆ… በቀን ያንተን ዘፈን ሳልሰማ አልውልም… በርታ…… 2ኛ አልበምህ ከዚህ በላይ እንደሚሆን አልጠራጠርም…. ባይ (ትልና ትሰናበታለች ሄለን የአክስቴ ልጅ ናት) ጋዜጠኛው;- ሌላ አድማጭ…. ሄሎ ማን እንበል…. ከዬት ነው? አድማጭ;- መስፍን ነኝ… ከአዳማ… ኤፍ አድናቂክ ነኝ. . . ሌላ አድማጭ…. አድናቂ…. ብዙ አደናቂ . . . ጋዜጠኛው;- ሌላ አድማጭ…… ሄሎ አድማጫችን… አድማጭ;- አቤ ከቤ ነኝ… ከአሰላ (ጉዴ ፈላ አልኩ) አቤ ከቤ;- ኤፍሬም ስለ አንቴ ብዙ ፈልጌ ነበር ላገኝ አልቻልኩም… (ምን ታሪክ አልኝ)…. ዝም ብዬ አንድ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ብሎ ዘረገፈው… ጋዜጠኛው;- አቤ… እናመሰግናለን መጨረሻ ላይ ሰብሰብ አድርገን ትመልሳለህ ኤፍሬም… ሌላ አድማጭ ሄሎ……. አድማጭ;-^^^^^^^^… ሄሎ … ^^^^^^^… ዮኒ ነኝ… ጋዜጠኛው;- ሬዲዮ ዝጋ እየረበሸን ነው? አድማጭ;- ሬዲዮ እኔ ጋር ዬለም…. ከጎረቤት ነው… (በጋራ ነው የሚሰሙን radio sharing)… ኤፍሬም ሰምቼክ አላውቅህም… ግን አንድ አንድ መሰረታዊ ጥያቄ ልጠይቅህ… (ስልኩ ተቋረጠ ቴክኒሻኗ ገላገለችኝ አላውቅህም ይላል እንዴ)… ጋዜጠኛው;-…. እሺ የአድማጫችን ስልክ ተቋርጦኋል… ሌላ አድማጭ… አድማጭ;- ሄሎ ኤፊ….ሀይማኖት እባላለው... ከቦሌ ቡልቡላ……በጣም አድናቂክ ነኝ::… ሙዚቃህን ሰምቼ አላውቅም…… በጣም አድናቂህ ነኝ………… (በለው ሰምታኝ ሳታውቅ አድናቂ ተመስገን ያ ዮኒ ከዚህ አይማርም) እና ጥያቄ አለኝ የምትወደው የከለር አይነት?.... አመሰግናለው… (እኔም አመሰግናለው) ጋዜጠኛው;- የአድማጮችን ጥያቄ ወደ በኋላ ላይ እንመለስበታለን አሁን ዬኔን ጥያቄ ላስከትል:: ትዳር እንደያዝክ አውቃለው እስቲ ስለ ትዳር አውራኝ? እኔ;- ok…….. ትዳር መስርቻለው ቤቲ ትባላለች (not big brother)………… በጣም ተፈቃቅደን….. ተቻችለን…….. ተነጋግረን……….. ነው የምንኖረው…….. ኦ…….. ቤቲዬ…….. I… love…. You…. So…. Much… በጣም ነው የምወዳት …………… (እውነታው ግን ከቤቲ ጋር ተጣልተን ከትናንት ጀምሮ ቤተሰቦቿ ጋር ነች) ጋዜጠኛው;- አሁን አንድ አርቲስት አየር ላይ ነው…………… ሄሎ አርቲስት እንትና…………. ኤፍሬምን እንዴት ትገልፀኋለክ ? አርቲስቱ;- ኤፊን……. ምን ብዬ ልግለፅልክ……………. ታታሪ….. ሰው አክባሪ…… በስራው ቀልድ የማያውቅ…….. ቀልደኛ…….. ታዛዥ…….. በቃ ኤፍሬምን እንዲ ነው ብዬ መግለፅ ይከብደኛል………. (ብሎ ቆልሎኝ ይወጣል እግዜር ይስጠው):: ጋዜጠኛው;- 2ኛ አልበምህ መቼ ነው የሚወጣው? እኔ;- 2ኛ አልበሜን ጨርሻለው::……………. ብዙ ታዋቂ ሰዎች ተሳትፈውበታል በግጥም………. ይልማ ገ/አብ……… 3 ዜማ ደግሞ ቴዲ አፍሮ………… ሰቶኛል ቅንብር እነ አበጋዙ…….. አማኑኤል……. ቴዲ ማክ……… ተሳትፈውበታል……. እኔም በግጥም እና ዜማ አለሁበት::…….. አሁን ማስተሩን ጨርሻለው…….. አዲካ ያሳትማል እንደሚታወቀው የcopy right ነገር ሀገራችን ላይ አስቸጋሪ ነው::……… እሱ እስኪረጋጋ እየጠበኩ ነው………… (እውነታው ግን ይልማን በአካል አግኝቼው አላውቅም……. ገና ግጥም እየሰበሰብኩ ነው……… ማስተሪንግ ያልኩት ብዙ ድምፃዊያን ስለሚሉ ነው) ጋዜጠኛው;- እሺ……… ኤፍሬም ቀጣዩ ስራህ እንደ በፊቱ አሪፍ እንደሚሆን ተስፋ…………… I hope አለኝ (በለው) 2ኛ አልበምህን አድምጫለው……….. በጣም አሪፍ ነው…………… እዚህ ድረስ መጥተክ ለሰጠህን ሰፊ የህይወት ተሞክሮ እናመሰግናለን::……….. አድማጮቻችን ካለን የሰአት እጥረት ምክንያት የእናንተን ጥያቄ ባለማንሳታችን ይቅርታ እንጠይቃለን::……….. ኤፍሬም በስተ መጨረሻ ምን ማስተላለፍ ትፈልጋለህ?......... እኔ;- የኢትዮፒያ ህዝብ በጣም አድማጭ ሆኖኋል አሪፍ ስራ ካልሰራክ አይቀበልህም ስለዚህ አሪፍ መስራት አለብን::………. ህዝቡም copy መግዛት ዬለበትም…………. ጥበቡን ማበረታታት አለበት……… ሁላቹንም ከልብ አመሰግናለው…….. ሰሞኑን ወደ አውሮፓ ቱር………… አደርጋለው ከዛ ስመለስ አልበሜ ይለቀቃል (ወይ መሄድ…………….ገጠር ዘመዶቼን ልጠይቅ ነው የምሄደው) ጋዜጠኛው;- የዛሬው እንግዳችን………. አርቲስት ኤፍሬም አማረ ነበር……….. ሳምንት ከሌላ አርቲስት ጋር እንመጣለን የጣቢያው ፕሮግራም አስከ ምሽቱ 6 ሰአት ይቀጥላል…………. እኛ ተሰናበትን…………. ቸው የጥላሁንን ሙዚቃ ጋብዤ እሰናበታለው……………
Posted on: Wed, 25 Sep 2013 09:11:37 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015