በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ - TopicsExpress



          

በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው #Ethiopia #Gonder የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ፫ኛ ዓመት የድግሪ ተማሪ የሆነው ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በፅንፈኛው ወያኔ አባላት በጩቤ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ሟች ወጣቱ ያነሳቸው የነበሩ ጥያቄወች በስፋት መነሳት ጀምረዋል :: ሟች አንተነህ ዘረኛው የወያኔ ወራሪ ቡድን በንፁሃን አማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዉስጥ አየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለፍርሃት ይቃወም የነበረ ሲሆን ደካማው የወያኔ ቡድን የለመደውን ደም ማፍሰስ ተግባሩን ፈፅሞበታል : ወጣቱ የተገደለው በጩቤ ተወግቶ ሲሆን እሬሳው ከዳሽን ብራ ፋብሪካ በስተጀርባ ተጥሎ ተገኚቷል :: የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ እሄን አስከፊ የሆነ የጠባቦች ድርጊት አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን ወነጀለኞችን በተገኙበት ለመቅጣት ያለ እረፍት ይሰራል ወጣቱ ከዚህ መማር ያለበት ነገር ቢኖር የወንድማቺን የአንተነህ እጣ ሳይደርሰው ወያኔን ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል በመቀላቀል የወገኖቻችን የስቃይ አመታት እናሳጥር በማለት መልክቱን ያስተላልፋል : ለሟች ቤተሰቦች መጥናናቱን ይስጥ !! የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ሰሜን ጎንደር
Posted on: Sun, 24 Nov 2013 19:55:07 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015