ባለፈው ሰሞን ጃዋር አጀንዳ የነበረ - TopicsExpress



          

ባለፈው ሰሞን ጃዋር አጀንዳ የነበረ ግዜ፣ አኔ ‹‹ኢትዮጲያ ሌላው ቀርቶ ከቤተሰቤ ትበልጣለች›› ብዬ ብጽፍ፤ አንዱ ቀረብ ያለ ወዳጄ ‹‹ድሮንም ከተማ አደጎች የማንነት ቀውስ አለባችሁ›› ብሎ በረጅሙ ሸነቆጠኝ - እዚሁ ፌስቡክ ላይ፡፡ እኔ ነገር ላለማባባስ ብየ ዝም አልኩ በወቅቱ፡፡ ግን ደግሜ ደጋግሜ ባሰብኩት ቁጥር እጅጉን ከነከነኝ፡፡ ከተሜው ‹‹ንጹህ እንትን›› (በደም ይሁን በአመለካከት) ባለመሆኑ እንደጥፋት ሊቆጠርበት ይገባል እንዴ? የዛሬ 8 ዓመት (ግንቦት/ሰኔ-1997) ኔሽን በሚባል የአማርኛ ጋዜጣ ላይ ‹‹የከተሜው ጥያቄ (The Urbanite Question)›› በሚል ርዕስ አስረግጬ ያስቀመጥኩትም፤ ኢሕአዴግ የከተማ-አደጎችን ስነ-ልቦና ታሳቢ ያደረገ አሠራር የመቀየስ ግዴታ እንዳለበት ነው(ያንን ጋዜጣ ለሚያገኝልኝ ወሮታውን እከፍላለሁ)፡፡ ባለፈው ዘመን ተጽዕኖ የደረሰባቸው ማንነቶች እንደነበሩ ጥያቄ የለውም:: ከኔ ዘመዶች እንኳን ሁለት ሶስት ያህሉ (በ1970ዎቹ አዲስ አበባ የመጡ) ደርግ ‹ወያኔ› እንዳይላቸው ፈርተው ስማቸውን ያሻሻሉ ነበሩ፡፡ ዛሬ እነሱ ሆነ ሌሎች ስለስማቸው ፍርሀት የለባቸውም - በዚያ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡ በተገላቢጦሽ ዛሬ ዳንኤል ‹ኢትዮጲያ ወይም ሞት› ለማለት ማመንታት አለበት እንዴ? ምነው ጎበዝ እንሰብ እንጂ? እኔ በበኩሌ አንድ ነገር ላስቀምጥ፡፡ ማሰብ አቅቷችሁ ብትበታተኑ - የኢትዮጲያን ፓስፖርት ይዤ የሆነ ሀገር ሄጄ እጠጋለሁ እንጂ ለአንዳቸሁም የሠፈር መንግስት ዕውቅና አልሰጥም፡፡
Posted on: Mon, 29 Jul 2013 22:31:30 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015