ነሃሴ 26 የሚካሄደውን ሰልፍ በማስመልከት - TopicsExpress



          

ነሃሴ 26 የሚካሄደውን ሰልፍ በማስመልከት በክ/ከተማ ደረጃ የመንግስት ሰራተኞች ዛሬም ተሰብስበው ዋሉ:: #Ethiopia #nehase26demonstration #AddisAbeba የፊታችን ነሀሴ 26 የሚካሄደውን ጸረ አክራሪነት ሰልፍ በማስመልከት የመንግስት ሰራተኞች በክ/ከተማ ደረጃ ዛሬም ተሰብስበው መዋላቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፤በስብሰባውም ወቅት ከሰራተኞቹ መካከል የሰልፉ አስተባባሪዎች የተመረጡ ሲሆን በየመንግስት መስሪያቤቱ አስተዳደር ቢሮ ከጠዋቱ 11.30 እስከ 12.30 ድረስ መገኘት እንዳለባቸው መመሪያ ተሰቷል፡፤ በመቀጠልም በተመረጡት ሰሰልፉ አስተባባሪዎች አማካኝነት የመፈክር እደላ የሚካሄድ ሲሆን መፈክር እደላው እንደተጠናቀቀ ወደ ሰልፉ ቦታ ጉዞ እንደሚጀመር ተገልፆል፡፤በስብሰባው ወቅት በተገለጸው መሰረት የሰልፉ ስነ-ስርአት ከጠዋቱ 3.30 ላይ ይጠናቀቃል መባሉን ምንጮች ዘግበዋል፡፡ በተያያዘም ዜና በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞችም በነቂስ በመውጣት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደሚሳተፍ እና የኢትዬጲያ ህገ መንግስት አክራሪነትን ቢፈቅድ እንኳን የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው ኢስላም ስለማይፈቅድላቸው ማንኛውንም አይነት አክራሪነት እንደማይቀበሉት ለማሳየት በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡
Posted on: Fri, 30 Aug 2013 19:21:19 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015