አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የናይጄሪያ - TopicsExpress



          

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የናይጄሪያ ቡድን ብቃት ከቡድናችን ይሄን ያህልም የላቀ አይደለም አሉ፡፡ 2 ለ 0 በተጠናቀቀው በባለፈው የአፍሪካ ዋንጫው ጨዋታ የተሸነፈው ቡድናችን በጨዋታ አልተበለጠም ብለዋል፡፡ “ያን ጨዋታ ልብ ብለህ ካየኸው ናይጄሪያ ከእኛ የተሻለ ቡድን እንዳልሆነ ይገባኻል” ብለዋል አሰልጣኝ ሰውነት ከልምምድ በኋላ ለጠየቃቸው የውጪ ሚዲያ ዘጋቢ፡፡ “በዛ ጨዋታ እስከመጨረሻው በጥሩ ሁኔታ ተጫውተን ልምዳቸውን ተጠቅመው በመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃዎች ባገኙት የፍጹም ቅጣት ምት ነበር ሊያሸንፉን የበቁት፡፡ አሁን ቡድናችን ብዙ ልምድ አግኝቷል ፣ በቀጣይ ጨዋታዎች ከናይጄሪያ ተሽለን እንጫወታለን” ብለዋል፡፡ አክለውም ብራዚልን ስለማላቃት ማየት እፈልጋለው ብለዋል። More Amharic News @ diretu.be/SB
Posted on: Thu, 10 Oct 2013 05:40:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015