አስደማሚ ከተሞች * Canada - የሀይቆች - TopicsExpress



          

አስደማሚ ከተሞች * Canada - የሀይቆች መናኸሪያ! በ Canada ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሀይቆች ይገኛሉ፡፡ * Mongolia - ጎረቤት ናፋቂዎች! በአማካይ በ Hong Kong በአንድ ስኩዌር ማይል ስፋት ውስጥ 340,000 ሰው ሲገኝ ፤ በ Mongolia ግን በአንድ ስኩዌር ማይል ስፋት ውስጥ 4 ሰው ብቻ ይገኛል፡፡ * Saudi Arabia - ወንዝ ናፋቂዋ! Saudi Arabia ምንም ወንዝ የላትም፡፡ አብዛኛውን ንፁህ ውሀ የምታገኘው ከከርሰ ምድር (ground water) ነው፡፡ * Niger - የታዳጊ ልጆች ሀብታም! በ Niger ግማሽ የሚያህለው ህዝብ (49%) ከአስራ አምስት አመት በታች ያለ ታዳጊ ነው፡፡ * Nauru - የብዙሀን ወፍራሞች መኖሪያ! በ Nauru ደሴት ከሚገኙ ህዝቦች መካከል ከ 95% በላይ ህዝብ ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ናቸው፡፡ * Papua New Guinea - ብዙ ቋንቋ የሚነገርባት! እንግሊዘኛ ብሔራዊ ቋንቋ ቢሆንም ከ1-2% የሚሆነው ህዝብ ብቻ እንግሊዘኛን መናገር ይችላል፡፡ አስገራሚው ነገር በPapua New Guinea ከ820 በላይ ቋንቋ መነገሩ ነው፡፡ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ወደ 12 % እንደማለት ነው፡፡ * Canada - የሀይቆች መናኸሪያ! በ Canada ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሀይቆች ይገኛሉ፡፡ * Canada - የብዙ የተማረ ህዝብ መኖሪያ! 50% ካናዳዊያን ምሩቃ ሲሆኑ ፤ እስራኤል 45% ጃፓን ደግሞ 44% ይከተሏታል፡፡ በእኛስ ሀገር ምን ያህል % ምሩቅ ነው? ምንጭ ፡- የእውቀት ማህደር ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ሼር በማድረግ አሳውቁዋቸው
Posted on: Tue, 05 Nov 2013 08:19:04 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015