እረኞች ምን አሉ? ኢትዮጵያውያን ፦ - TopicsExpress



          

እረኞች ምን አሉ? ኢትዮጵያውያን ፦ በዚህ እሳት በሆነው የኑሮ ውድነት መሃል ጥቂት ደመወዛችሁ እንዴት ሊበቃችሁ ቻለ? በተለይ በከተማ የምትኖሩ ኑሮውን እንዴት ተቋቋማችሁት? ወር ጠብቆ በሚመጣው ገንዘብ የትኛውን ጉድለታችሁን ትሞሉበታላችሁ? ለየትኛው ለህይወት አስፈላጊ ቁስ አዋላችሁት? የቤት ኪራይ ስትከፍሉ ምን ያክል ቀራችሁ? ለአንድ እንጀራ 3 ብር እያወጣችሁ ምን ተረፋችሁ? ለ1ሊትር ዘይት 50 60 ብር እያወጣችሁ ስንት ተረፋችሁ? በርበሬ ገዛችሁ? የታክሲውን ሮሮስ እንዴት ታገሳችሁት? የትምህርት ወጪ ያለባችሁ ከሆነስ እንዴት ከፈላችሁት? ልጆች ያላችሁስ ወጪያቸው ከበዳችሁ? ታማችሁስ ከሆነ ውድ የሆነው የህክምና ወጭውን ማን ሽፈነ? የታዘዘላችሁን መድሃኒትስ ተወዶባችሁ ሳትገዙት ተመለሳችሁ ወይንስ የቻይና በርካሽ አገኛችሁ? ልብስ ከቀየራችሁ ስንት ጊዜ ሆነ? ቤተሰብስ ትረዳላችሁ? ተቀማጭስ ይኖራችኅል? የሻይ መጠጫስ በኪሳችሁ አልተረፈም? የቤት ኪራይስ አልጨመረባችሁም? ወዳጆች ፦ ይህ ሁሉ ድካም ፡ ይህ ሁሉ ብሶት ፡ ይህ ሁሉ ጭንቀት ወዴት እንድታመሩ አነሳሳችሁ? ሚዛን እንድታጭበረብሩ ግድ አላችሁ? ወይንስ በድሃ ላይ እንድትጨክኑ አረጋችሁ? በሙስና እንድትቆሽሹ ተዘጋጃችሁ? ወይንስ ለገንዘብ ግፍ እንድትሰሩ ምክንያት ሆናችሁ? በነጋዴወች ላይ ጥላቻ አደረባችሁ? ወይንስ እግዚአብሄርን አማረራችሁ? ሃገራችሁን እንድትጠሉ አበቃችሁ? ወይንስ ከሃገር ለመሰደድ ግድ አላችሁ? ማጅራት መምታት ከጀላችሁ? ወይንስ ሰርቆ ማምለጥን አሰባችሁ? ኢትዮጵያውያን ፦ ሃዘናችሁ በበዛ መጠን እግዚአብሄርን አመስግኑ ፤ ማጣታችሁ በቀረበ መጠን ፡ ደሃን ጠርታችሁ አጉርሱ ፤ ተስፋ ባጣችሁ መጠን ፡ ወደአምላክ ፊታችሁን አቅኑ ፤ ጤናችሁ በተቃወሰ መጠን ፡ ለፀሎት ወደመቅደስ ገስግሱ ፤ ብቻችሁን የሆናችሁ በመሰላችሁ ጊዜ አምላክን ጥሩት ፡ አፅናኝ ያጣችሁለት ፡ አፅናኙን ጥሩት ፤ እንባ ባይናችሁ በሞላ ወቅት እንባን አባሹን ና በሉት፡፡ ማጣት ስርቆትን ቢያስከትል ፡ እናንተ ግን ከምትሰርቁ በርሃብ ሙቱ ፤ መጠቃት ብሶትን ወልዶ ክፋትን ከምታስቡ ፡ ስለአምላክ ብላችሁ ሁሉን ይቅር በሉ ፤ ሳትታክቱ ጠንክራችሁ ስሩ ፡ ሳትሰለቹ ድከሙ ፡ አይናችሁን ተቆጣጠሩ ፡ ልባችሁ ያለበትንም ቦታ መርምሩ ፤ በአቋራጭ ሃብት ያገኙትን አትመልከቱ ፡ የሃጢአተኛውንም ከፍ ከፍ ማለት አትመኙ ፡ የክፉወችም አብቦ መታየት አያስጎምጃችሁ ፤ ከፍ ያለው ለመውደቅ ነው ፡ ማበቡም ለመርገፍ ነውና፡፡ ወዳጆች ሆይ ፦ በድህነት ውስጥ ብትኖሩ ከእናንተ የደከሙትን አስቡ ፤ ሆዳችሁ ምግብ ቢራብ ፡ ከቀመሱ ብዙ ቀን የሆናቸውን እየጠራችሁ አጉርሱ ፤ ልብሳችሁ እያረጀ እየገፈፈ በሄደ ጊዜ የድሃውን መታረዝ እያሰባችሁ አልብሱ ፤ ኑሮ ቢያጎብጣችሁ ፡ ትሁታን ሆናችሁ ዝቅ ያሉትን ቀና አርጉ ፤ ዘወትርም ጠንክሮ ለመስራት አትለግሙ፡፡ መልካም አዲስ አመት!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
Posted on: Fri, 20 Sep 2013 19:20:06 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015