እንተዋወቀው!!! በአሁኑ ሰአት በሂጂራ - TopicsExpress



          

እንተዋወቀው!!! በአሁኑ ሰአት በሂጂራ ኮምፓውንድ(ቂልንጦ) በእስር ላይ ከሚገኙት ብርቅዮ ልጆቻችን አንዱ የሆነው የጂማ ዩኒቨርሲቲይ ተማሪ የአብዱ መሀመድ የህይወት ታሪክ በአጭሩ በ 1983 አ.ል መስከረም 10 ረቡእ ቀን ከኢሻ ሰላት በሗላ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ ተወለደ በዚያው ወረዳ ደጋን ከተማ አካባቢ እድሜው ለትት ሲደርስ በ 1990 አ.ል በደጋን አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት|ቤት ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትቱን እዚያው አጠናቀቀ። የ8ኛ ክፍል የማጠናቀቂያ ፈተና ወስዶ በ 76 ነጥብ አማካይ ውጤት (91%) በማምጣት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት|ቤት ተዘዋወረ 1998አ.ል ጀምሮ የሁለተኛ ደረጃ ትቱን በደጋን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት|ቤት ተከታትሎ 10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ውጤት 3.4 በማምጣት ወደ መሰናዶ ት|ቤት ተዘዋወረ። የመሰናዶ ትቱን የተከታተለው 2000 አ.ል በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳ ባቲ ከተማ በሚገኘው ባቲ ቄይ መስቀል77 2ኛ እና መሰናዶ ት|ቤት ሲሆን በ 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ|entranc e ፈተና 280|500 በማምጣት በጂማ ዩኒቨርሲቲይ የኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ department ተመደበ። 2002አ.ል ወደ ጂማ ዩኒቨርሲቲይ የከፍተኛ ትቱን ለመከታተል ሄደ በጂማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኮምፒውተር ሳይንስ department ተመደበ። የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤቱ 3.44 በማምጣት 2005 አ.ል በአጠቃላይ 3.2 አማካይ ውጤት ነበረው፤ ዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ የነበር ቢሆንም ቅዳሜ ጥር 1855 አ.ል ከቀኑ 6፡00 አካባቢ በደህንነቶች እና በጅማ በዩኒቨርሲቲ ኢንስፔክተር አማካኝነት ተይዞ በፍርድ ቤት ማዘዣ የሽብር ፈጠራ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ ከምሽቱ 6፡15 አከባቢ ማእከላዊ (በፌደራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ) ገባ። አላህ ይርዳው!!! አላሁ አክበር!!! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና ገጻችንን ላይክ ያድረጉ ድምፃችን ይሰማ በአዛን አንቲ-አህባሽ https://facebook/azan.anti ይህ ብሶት የወለደው የናንተው ልሳን ነው!!! አላማዬ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ውስጥ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ነው:: ይህ ፔጅ በወቅታዊ የሙስሊሞች ጉዳይ ዙሪያ ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ለናንተው ያቀርባል:: ፖለቲካም ሳይዳሰስ አይታለፍም::
Posted on: Wed, 24 Jul 2013 11:03:31 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015