ከሰሞኑ የኖርዌዩ ጠቅላይ ሚኒስትር - TopicsExpress



          

ከሰሞኑ የኖርዌዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ለግማሽ ቀን ማንነታቸውን ደብቀውና ‹‹ተራ ሰው›› መስለው ታክሲ ሲነዱ ውለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ለምን እንዲህ አደረጉ ሲባሉ ‹‹በመስከረም ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ‹‹ተራውና ተርታው›› ህዝቤ ያለምንም መሳቀቅ የሆድ የሆዱን እንዲያጫውተኝ አስቤ ነው›› ብለዋል፡፡ ይህን ዜና የሰሙ የሀገሬ ሰዎች፤ ‹‹ምናለ የኛም መሪዎች አንዳንድ ቀን እንኳን ‹‹ተራ ሰው ››መስለው ‹‹የተራውን ህዝብ›› የልብ ትርታ ቢያደምጡ›› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ መቼስ እኛ ሰርክ መሪዎቻችንን መንቀፍ ስለሚቀናን ነው እንጂ፤ የኛ መሪዎች እኮ ሁሌም ‹‹ተራ ሰዎች›› ናቸው፡፡
Posted on: Tue, 13 Aug 2013 09:54:53 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015