ከስራ ወጥቼ የተለመደውን ረጅም የታክሲ - TopicsExpress



          

ከስራ ወጥቼ የተለመደውን ረጅም የታክሲ ሰልፍ ተሰልፊያለሁ፡፡በፊት በፊት የሰልፉ ርዝመት ያማርረኝ ነበር አሁን ግን ለምጀዋለሁ እንዲያዉም አሁን አሁን በጄ የሚነበብ ነገር ይዤ መሰለፍ ስለጀመርኩ ሰልፉ እያጠረብኝ ተቸግሬአለሁ፡፡የሆነ ሆነና እነሆ ዛሬም ተሰልፌአለሁ ከፊት ለፊቴ እነድ በእድሜ ገፋ ያሉ ቄስ ከሳቸው ፊት ደግሞ ወጣትነቷን ያጋመሰች ሙሉ ጥቁር ልብስ እና ጥቁር ሂጃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ተሰልፈዋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ቄሱ እና ሙስሊሟ ሴት የተጫወቱትን፣ እኔም የማነብ መስዬ የሰማሁትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ ቄስ፡- የኔ ልጅ ፆም እንዴት ነው? ልጅት፡- ጥሩ ነው አባት ቄስ፡- ታዲያ ሰአቱ አልደረሰም (የማፍጠሪያ ሰአት ማለታቸው ነው)? //ሰአቴን አየሁ 11፡56 ይላል// ልጅት፡- አዎ እየደረሰ ነው እኔም ወደቤት እየሄድኩ ነው ቄስ፡- አይ ይሄን ሁሉ ሰልፍ ልጠብቅ ካልሽማ አንድ ሰአትም አትደርሺ፡፡ ለምን ወደፊት ሄደሽ ልጆቹን(ተራ አስከባሪዎቹን) እንዲያስቀድሙሽ አትጠይቂም? ልጅት፡- እሺ ይላሉ ብለው ነው? ቄስ፡- (ቆጣ ብለው) እንዴ ለምን እሺ አይሉም ኢትዮጵያዊ አይደሉም እንዴ? ግድ የለም ሂጂ ጠይቂያቸው እኔ፡- ሞክሪ እምቢ የሚሉ አይመስለኝም በሁለት ቲፎዞ የልብ ልብ የተሰማት ልጅ ወደፊት ሄዳ ከአንዱ ተራ አስከባሪ ጋር ማውራት ጀመረች፡፡ ተራ አስከባሪው እሷ ከፊት እንድትሆን ነግሯት ሌሎች በአለባበሳቸው ሙስሊም ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን ከየሰልፉ እያስወጣ ወደፊት ይልካቸው ጀመር፡፡ ሰልፍ የሚጠብቀውም ሰው እንኩዋን ሊቃወም እንዲያውም አንዳንዱ የቀረ ሰው እንዳይኖር ዞር እያለ በአይኑ ይፈልግ ነበር፡፡ በእንዲህ የተሰባሰቡት ሙስሊሞች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው አንድ ሙሉ ታክሲ ሆንው እልም!!! ቄሱ እንዳሉትም የታክሲ ተራ አስከባሪዎቹም፣ የታክሲ ተራ ጠባቂዎቹም፣ ኢትዮጵያዊ ነበሩ!!! እንዲህ ነው መተሳሰብ!!! እንዲህ ነው መከባበር!!! አቦ ይሄን መከባበር እና መተሳሰብ ከታክሲ ሰልፍ ወደ ላይም ከፍ ያድርግልን!!
Posted on: Mon, 05 Aug 2013 18:47:06 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015