ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ የተላለፈ ወቅታዊ - TopicsExpress



          

ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ የተላለፈ ወቅታዊ መልእክት 📩 ‌ —ታላቁ ህዝብ— ካነበቡ 📝 በዋላ ሼር በማድረግ ያሰራጩ ✳ “ከማንዴላ የአፓርታይድ የነፃነት ትግል በኋላ አፍሪካ ውስጥ የተደረገ የነፃነት ትግል ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያደረጉት ሰላማዊ ትግል (non-violence protest) ነው፡፡” እውቋ የሚዲያ ሰው Operah. ‌ መንግስትንና ህዝበ ሙስሊሙን በቶምና ጀሪ የመሰለችው ጸሐፍት ማን ነበረች? የህዝበ ሙስሊሙን የተቃውሞ ስልትና ብልጣብልጥነት በጥበበኛዋና ሁሌም አሸናፊ በሆነችው ጀሪ፣ የመንግስትን አንባገነንነትና ግብዝነትን በቶም መስላ ያስነበበችው መጣጥፍ አግራሞቴን ስቦታል፡፡ አዎን ስለዚህ ታላቅ ህዝብ ለወደፊት ብዙ የምንለው ይኖረናል፡፡ ‌ እኛን እስር ቤት ለመጠየቅ የሚመላለሰው ሰፊው ህዝብ “እናንተ የኛ ጀግኖች ናችሁ” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ አደባባይ በሚያደርጉት ተቃውሞ ላይ “መሪዎቻችን ይፈቱ” ሲል መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ‌ ህዝቤ ሆይ! የእናንተ አይነት ጀግኖች ኢትዮጵያ አይታ አታቅም፡፡ እናንተ ተከታዮች ሳትሆኑ የእኛ መሪዎች ናችሁ፡፡ ከእኛ በላይ ለመብት ትግሉ መስዋእትነት የከፈላችሁ እናንተው ናችሁ፡፡ ‌ በአጭሩ የዊክሊክሱ መስራች ያለውን ቃል መጠቀም ይቀለኛል፡፡ ግለሰቡ የተለያዩ የተደበቁ ሚስጥሮችን ይፋ በማድረግ የአለምን አግራሞት ስቧል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞችም ጀግና መሆኑን ደጋግመው መስክረውለታል፡፡ እርሱ ግን የግብፅ ወጣቶች አደባባይ ላይ ወጥተው የከፈሉትን ተጋድሎ ሲመለከት እንዲህ አለ፡- ‌ “I am not the hero, the Heros are, those who are in the street” “እኔ ጀግና አይደለሁም ጀግኖች አደባባይ ላይ የወጡት ናቸው” እኛም ይህንኑ ነው የምንለው፡፡ ጀግኖቹ እናንተው ናችሁ፡፡ ‌ source: BBN RADIO
Posted on: Mon, 21 Jul 2014 19:45:36 +0000

Trending Topics



HOW TO GENERATE LEADS FAST ON FACEBOOK FROM ANY BUSINESS

Recently Viewed Topics




© 2015