ወንድሞቻችንን የመዘየር ዘመቻ #Ethiopia - TopicsExpress



          

ወንድሞቻችንን የመዘየር ዘመቻ #Ethiopia #Ethiomuslims ከ 10 ወር በፊት ከከሜሴ ከተማ ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙት ወንድሞቻችን ወደ ደሴ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረው ጉዳያቸው በደሴ ፍ/ቤት እየታየ ይገኛል፡፡ መስከረም 24/2006 በነበራቸው ቀጠሮ ላይ ቢቀርቡም ፋይላቸው በወጉ እንኳን ሳይታይና የተከሰሱበት ጉዳይ ሳይነገራቸው ለጥቅምት 13 ተቀጥረው ወደ ማረሚያ ቤት ተመልሰዋል፡፡ እናም ወንድሞቻችን ይሄንን ሁሉ ስቃይ ለዚህ ይህል ጊዜ የሚያዩት ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ እንጂ ወንጀል ኖሮባቸው አይደለም፡፡ ስለዚህ የደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከእነዚህ ንፁሃን ወንድሞቻችን ጎን ልንቆምላቸው ግድ ይላል፡፡ ስንቅን በተመለከተ በቀን በቀን ሚስቶቻቸው ከከሚሴ ደሴ በሴት አቅማቸው እየተመላለሱ ስንቅ በማድረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ የደሴ ሙስሊም ማህበረሰብ እነዚህን ፍትህ የተነፈጋቸውን ሙስሊም ወንድሞቻችንን እየሄድን በመዘየር አብሽሩ ልንላቸው ይገባል፡፡ እኛ የደሴ ሙስሊም እነሱን ሄዶ በመዘየር ቢያንስ ስንቃቸውን በመሸፈን የቤተሰቦቻቸውን ቀን በቀን መመላለስ ልናስቀር እንችላለን፡፡ የደሴ ሙስሊም ምንም ዓይነት ቅስቀሳ ሳያስፈልገው ቀድሞ ታስረው የነበሩትን ወንድሞቻችንን በሰልፍ ሲዘይር ኖሯል፡፡ እናም እነዚህንም ወንድሞቻችንን ካጠገባቸው በመሆን አለንላችሁ ብንላቸው ለነሱም ሞራል ነው ለእኛም አንድነታችንን የምንገልጽበት ጥሩ መንገድ ይሆንልናል ኢንሻአላህ! ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ ድል ፍትህ ለተጠማው ሙስሊም አላሁ አክበር
Posted on: Sat, 05 Oct 2013 17:29:45 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015