ዛሬ መንግስት ራሱ በጠራው ስብሰባ - TopicsExpress



          

ዛሬ መንግስት ራሱ በጠራው ስብሰባ በሙስሊሙ እና በክርስቲያኑ አንድነት ሐፍረት ተከናነበ!! በዛሬው እለት 9/12/2005 የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ሙስሊም እና ክርስቲያን ነዋሪዎች በሐይማኖት መቻቻል ዙሪያ አማኑኤል አካባቢ በሚገኘው ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ስብሰባ ተደረገ። በስብሰባው ከመድረኩ የተለመደው የሐይማኖት መቻቻል ዲስኩር በሰፊው ከተብራራ በኋላ ዋና አላማቸው የነበረውን የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ማስከበር ትግል ጥላሸት በመቀባት ሂደቱን የአክራሪነት እና አሸባሪነት ምንጭ እና ምክንያት አድርገው ፈርጀውታል። ከመድረኩ በሚነዛው አሉባልታ የተማረረው ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ተሳታፊ በአንድ ድምፅ "ይሄንንማ በኢቴቪ ሰምተን ሰልችቶናል" በማለት መድረኩ ላይ ለነበሩ ካድሬዎች አሳፍሯቸዋል። ካድሬዎቹ ተደናግጠው ቀጥታ ወደ ጥያቄ እና አስተያየቶች ለተሳታፊው ሲጋብዙ። ሁሉም በአንድ ድምፅ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝሯል። ለአስተያየት እድል የተሰጠው የአንዋር መስጂዱ የጥበቃዎች ሃላፊ እና የወረዳው ነዋሪ አቶ ሸምሱ አባስ ታጣቂዎች በኢድ ቀን በሙስሊሞች ላይ የወሰዱትን ጥቃት አድንቆ መንግስት አጠናክሮ እርምጃውን መቀጠል እንዳለበት እና ከጎኑ እንደሚቆም ተናገረ፤ በአቶ ሸምሱ ንግግር የተበሳጩት በአዳራሹ የተሰባሰቡት ክርስትያን እና ሙስሊም ተሳታፊዎች ለነግግሩ አፀፋዊ መልስ ሰጥተዋል። አንድ ክርስቲያን የወረዳው ነዋሪ "እኔ በመንግስት ድርጊት ተበሳጭቻለው ህገ-መንግስቱ ይከበር ላሉት እንዴት ዱላ ይበረክትላቸዋል ትላለህ የተጎዱት እኮ ሰላማዊ እና ሕጋዊ ወንድሞቻችን ናቸው መንግስት ቆም ብሎ አካሄዱን ሊያጤን ይገባል" በማለት ሃሳብ ሰንዝረዋል። ሌላው ክርስቲያን ደግሞ "መንግስት ራሱ ነው ጥፋተኛ አሕባሽ የተባለውን ሐይማኖት በሙስሊሙ ላይ በግድ ለመጫን ፈልጎ ነው ይህ ሁሉ የሆነው" ሲል በምሬት ተናግረዋል። መንግስት የጀመረው ክርስቲያኑን እና ሙስሊሙን የማጋጨት እና የሙስሊሙ ትግል ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ነው፣ የአክራሪዎች፣ የጥቂቶች እና የአሸባሪዎች ጥያቄ ነው የሚለውን የመንግስት ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ እንዳልሰራ የሚጠቁም ክስተት እንደሆነ የዛሬው የወረዳ 3 ስብሰባ አስመስክሯል!! ድል ፍትሕ ለተጠማው ሕዝብ!!
Posted on: Thu, 15 Aug 2013 12:21:24 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015