የEU እና የኖርዌይ ባለስልጣኖች (The Human - TopicsExpress



          

የEU እና የኖርዌይ ባለስልጣኖች (The Human Rights and Democracy Sub Group in Ethiopia) ከተቃዋሚ አመራሮች ጋር በሰብዓዊ መብት፣ በፖለቲካ እስረኞች፣ በስደተኞች፣ በሲቪክ ማህበራትና በሚዲያ አፈና ስለሚከሰቱት ችግሮች የተወያዩበት ቃለ ጉባኤ ዛሬ ደርሶኛል። የጉዳዩ አሳሳቢነት በቅርብ ጊዜ ታትሞ በሚወጣው የለጋሽ ሃገሮች ግሩፕ በኖቬምበር 2013 በጀመሩት የጥናት ሪፖርት ላይ ከባድ በሆነ አገላለጽ እንደሚወጣ ያወሳል። የምርጫ 2015 ላይ ያተኮረው በኖርዌይና የአውሮፓ ህብረት የሚመራው የዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ሪፓርት በሰኔ ወር የሚያልቅ ሲሆን የአውሮፓ ሃገራት በሚቀጥሉት አመታት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸው ዲፕሎማሲያዊ እና የጋራ ስምምነቶች በዚሁ ሪፖርት ውጤት ላይ የሚመኩ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Posted on: Tue, 15 Apr 2014 04:37:45 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015