የምስራቅ አፍሪካ ፍዳ ደሞ ምን - TopicsExpress



          

የምስራቅ አፍሪካ ፍዳ ደሞ ምን ተቀምሞልን ይሆን?? በዚህ ሳምንት አሽ ካርተር የተባሉት የአሜሪካ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ከኢስራእል ጀምረው ዩጋንዳን እና ኢትዮጵያን ሊገበኙ ተነስተዋል::እስራኤል ገብተው አስፈላጊውን ሴራ ካሴሩ በኋላ በአንድ እርከን ከሚበልጧቸው ከአቻቸው ከኢሁድ ሻኒ ጋር ራታቸውን በልተው ሲጠግቡ ፍዳ ወደታቀደላት ምስራቅ አፍሪካ ይበራሉ:: ምስራቅ አፍሪካ እንደደረሱ ከዩጋንዳ ከፍተኛ የደህነንት እና የመከላከያ ባለስልጣናት ጋር የአከባቢውን ደህንነት በተመለከተ አስፈላጊውን ውይይት ያደርጋሉ:: አሁን አሜሪካ ስለኛ ክልል ደህንነት ምናገባት? የራሷን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ቅጥረኛ የሆኑ አምባገነን መሪዎችን መንከባከብ አይዟቹ ማለት ስራዬ ብላ ተያይዛዋለች:: ዩጋንዳን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ሲመጡ ታዲያ እንደ እስራኢል እና ዩጋንዳ አቻዎቻቸውን ሳይሆን የሚያገኙት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር..ስለመከላከያ እና ደህንነት ግንባታ አሸባሪነትን በመዋጋት ስለሚደረገው ድጋፍ ይወያያሉ:: በጋራ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ:: የሰውየው ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ምነው አሸባሪነት ላይ አተኮረ አሸባሪ መፈልፈያ አይደለንም እኮ ለወያኔ መንግስት አስፈላጊውን ማበረታቻ በመስጠት ዜጎችን እንዲፈጅ የሚያደርጉ ሃያላን መንግስታት መች ነው ከላያችን የሚወርዱት :: ኢስራኤል እና ዩጋንዳ ያላነሱትን ጉዳይ እዚህ ማንሳት ምን አስፈለገ አሜሪካ እየሰራች ያለችው ደባ እየቀመመች ያለችው መርዝ እየቀበረች ያለችውን ቦምብ በጥንቃቄ ልናውቀው ይገባል::
Posted on: Tue, 23 Jul 2013 02:59:30 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015