የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ - TopicsExpress



          

የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ለሰባት ዓመታት እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ እዚያው ወኅኒ ውስጥ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቪኦኤ ገለፀዋል፡፡ ፖሊስ የሰጠውን ማስረጃ አይተናል ያሉት እስከፍርዱ ድረስ ከይግባኝ በፊት ቆመውላቸው የነበሩት ጠበቃ አቶ ጥላሁን ታደሰ ኢንጂነር ተስፋሁን ያረፉት ባለፈው ዓርብ ሌሊት መሆኑን አመልክተው የፖሊሱ መረጀ እራሣቸውን ማጥፋታቸውን እንደሚጠቁም ጠቁመዋል፡፡ ኢንጂነር ተስፋሁን እራሣቸውን አጥፍተዋል የሚለውን መግለጫ ለማመን እንደሚቸገሩ የሚናገሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ሕክምና እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበረና የጠየቁትን አለማግኘታቸውን እንደሚያውቁ፤ ከእህታቸው ጋርም በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረ ቤተሰብ እንደነገራቸው ገልፀዋል፡፡ ከወኅኒና ሌሎችም ባለሥልጣኖች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለዛሬ ባይሳካም ሙከራችን ይቀጥላል፡፡ ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ amharic.voanews. com/ content/ ethiopia-tesfahu n-chemeda-died- in- prison-08-26 -13/ 1737474.html
Posted on: Mon, 16 Sep 2013 04:36:24 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015